“ጋዜጠኞቹን ያሰረው ፌዴራል ፖሊስ ነው”

Views: 115

ትላንት ዓርብ ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የታሰሩትን ሁለት ጋዜጠኞች በቁጥጥር ሥር ያዋለው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሳይሆን፤ የፌዴራል ፖሊስ መሆኑን ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን አስታወቁ፡፡

ጋዜጠኞቹ በፍርድ ቤት ቅጥር-ጊቢ ውስጥ ጎላ ብሎ የማይታይ ምስልና ድምጽ የሚቀርጽ መሣሪያን ተጠቅመዋል በሚል ፖሊስ በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራ እያከናወነ ነው ሲሉ ለዘጋቢያችን አብራርተዋል፡፡

በትላንትናው እለት ለእስር ከተዳረጉት አንዱ የሆነውን የኢትዮጲስ ጋዜጣ ዘጋቢ ምስጋን ጌታቸውን ለማየትና ለማነጋገር እንዳልተፈቀደለት የተናገረው የጋዜጣው ሥራ አስኪያጅ እስክንድር ነጋ፣ አዳም ወገራ-ን ግን ትላንት 11፡00 ሰዓት አካባቢ ፖሊሶች ፈቅደውልኝ አግኝቸዋለሁ፡፡

“አዳም እንደነገረኝ፣ ሁለቱም የተወነጀሉት በፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ቀረፃ አድርጋችኋል በሚል ነው፡፡ ሆኖም፣ ሁለቱም በችሎት ውስጥ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን፣ የፖሊሶቹ ምርመራ ሁሉ በፍርድ ቤት ዘገባ እና ፍርድ ቤቱን ቀርጸኃል በሚል ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ ጥያቄዎቻቸውና ምርመራቸው ከአዲስ አበባ ባላ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ጋዜጠኛ ምስጋናው ደግሞ የባላደራ ምክር ቤት አባል አይደለም በማለት ለዘጋቢያችን ገልጿል፡፡

ትላንት ማምሻውን ፖሊስ ለታሳሪዎቹ ምግብ እና ልብስ እንዲገባላቸው መፍቀዱን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማቅረብ ሲንቀሳቀሱ አስተውለናል፡፡

ፖሊስ ጋዜጠኞቹን ሆን ብሎ ዓርብ ከሰኃት መያዙ፣ ከፍርድ ቤት እውቅና ውጪ እስከ ሰኞ በማቆየት ጫና ሊፈጥርባቸው ይችላል፤ ይህ የተለመደ የፖሊስ ሕገ-ወጥ አሰራር ነው ሲሉ ቤተሰቦች ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

በፍርድ ቤት የዘገባ ሥራ ላይ የነበሩት ጋዜጠኞች ሲቭል በለበሱ ፖሊሶች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትላንት 6፡00 ሰዓት ላይ ተወስደው ለእሥር መዳረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com