“ጥቁር ሽታ” መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል

Views: 851

በመዝናኛው ዘርፍ በአዲሰ ነገር ጋዜጣ  እንዲሁም በአሁን ሰዓት በፍትሕ መጽሔት ላይ በሥሙ፣ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ደግሞ በብዕር ስሙ ‹‹ሶፎኒያስ አቢስ›› በሚል የተለያዩ ወጎች፣ አጫጭር ልብወለዶችን እና መጣጥፎችን ለረዥም ጊዜ በመፃፍ ይታወቃል- መሐመድ ነስሩ፡፡

አሁን ደግሞ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ፣ ሥነ-ልቦናዊ እና ስነ-አእምሮ (ከአእምሮ ህመም) እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከዚህ ቀደም በጋዜጦች ላይ የጻፋቸውን እና ሌሎች አዳዲሰ ሃሳቦች በማካተት አንድ መድብል ለሕትመት አብቅቷል፡፡

ሙሐሙድ ነስሩ (ሶፎኒያስ አቢስ) በተለይም የአእምሮ ሕመምን በተመለከተ ‹‹ጥቁር ሽታ›› እና ‹‹እናትን ፍለጋ›› የሚሉት ጽሑፎችን በመጽሐፉ ውስጥ ማካተቱን ለኢትዮ-ኦንላይ አስታውቋል፡፡

ከአእምሮ ህመም ጉዳይ ጋር በማሕበረሰባችን፣ ሰዎች ሲሳደቡ ወይም ሲታረቡ እንሰማን፤ በተለያዩ ፊልሞች አእምሮን በሚነካ መልኩ ሲሰራ እናያንለን፤ ይህም የግንዘቤ ችግር በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ጽፌያለሁ ሲል ተናግሯል፡፡

የእምሮ ህመም ላይ መፃፍ ቀላል ነገር ባለመሆነም፤ ጥናት በማድረግ እና በአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት፤ እንዲሁም ባለሙያ በማማከር ጥንቃቄ አድርጎ እንደፃፈው መሐሙድ ነስሩ ነግሮናል፡፡

‹‹ጥቁር ሽታ›› መጽሐፍ በ203 ገጽ የተሰናዳ ሲሆን፣ በ120 ብር በገበያ ላይ ውሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com