በኢትዮጵያ በወርቅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው የሲፕረስ ኩባንያ በዓመት ከ47 ሚሊዮን ግራም በላይ ድፍድፍ እንደሚያመርት አስታወቀ

Views: 128

ከፊ ሚኒራልስ የተባለው ዓለማቀፍ ኩባንያ፣ በአሁኑ ጊዜ በምዕራብ ኢትዮጵያ ቱሉ ካፒ ዘጠና አምስት ከመቶ ድርሻ ወስዶ የወርቅ ማውጣት ሥራ እየሠራ ሲሆን፣ ከብድር ጋር የተያያዙ የገንዘብ አሠራሮቹን ማሻሻሉን ይፋ አድርጓል፡፡ በዓመት 47.6 ሚሊዮን ግራም ድፍድፍ እንደሚያመርትም ይጠበቃል፡፡

ሸር ካስት የተባለው ገፀ ድር እንዳስነበበው፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በስፋት እየሠራ ነው፡፡ ኩባንያው የገንዘብ አስተዳድር አሠራሮቹን ማሻሻሉ ለአሠራር ምቹ፣ ቀልጣፋ እና እንደ ሁኔታዎቹ ተለዋዋጭ እንደሚያደርገው ዘገባው አስታውሷል፡፡

ኩባንያው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ውል የተፈራረመው እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2015 ዓ.ም ሲሆን፣ ስምምነቱ የ20 ዓመታት ኮንትራት ነው፡፡

በአካባቢው እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ1930ዎቹ የጣሊያን ኩባንያ የወርቅ ፍለጋ ሥራውን ጀምሮ ነበር፡፡ በአካባቢው ወርቅ መኖሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተረጋገጠውም በጣሊያኑ ኩባንያ ነው፡፡

ከፊ ሚኒራልስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ በአሁኑ ጊዜ ሁለት ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ነው፡፡ እነርሱም አንደኛው እና ከፍተኛ የሥራ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት በኢትዮጵያ የሚገኘው የቱሉ ካፒ የወርቅ ፍለጋ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አርባ ከመቶ ድርሻ የሚወስድበት እና በሳውዳረቢያ የሚገኘው የጂባል ኩትማን የወርቅ ፍለጋ ፕሮጀክት ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com