የሳንፍራንሲስኮ ነዋሪዎች ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

Views: 121

በአሜሪካ፣ ሳንፍራንሲስኮ የቤይ እና አካባቢዋ የፖለቲካው ማኅበረሰብ አባላት፣ ወላጆቻቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የሶከር ስፖርት መጫወቻ ቁሳቁስ ሊለግሱ ነው ተባለ፡፡

ድጋፉ የሚደረገው በቅርቡ የቤይ ሀገረ-ግዛት ፕሬዚደንት ኢርኔ ሮዝ ወላጅ አልባ ሕፃናትን በጎበኙበት ወቅት ቃል በገቡት መሠረት ነው፡፡ ፕሬዚደንቱ ለቤይ ነዋሪዎች ያቀረቡት ጥያቄም ከተጠበቀው በላይ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቷል፡፡ የስፖርት ቁሶችን ለማሰባሰብም የሶከር ስፖርት ተጫዋቾችን ጨምሮ ሰፊ ተነሳሽነት ሎሰ አልቶስ የተባለው የሶከር ስፖርት ክለብ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጋቪን የተባለው የ16 ዓመት የሶከር ተጫዋች ቁሳቁሶችን ለመሰብሰብ ተነሳሽነት እንዳለው አብራርቷል፡፡ ድጋፉን እንዲያደርጉ ከተጠየቁት መካከል 50 ሰዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ከተጠበቀው በላይ የሶከር ስፖርት ቁሳቁስ ተሰብስቧል፡፡ ከተሰበሰቡ ቁሳቁሶች መካከል የሶከር ኳስ እና ካስማዎች ይገኙበታል፡፡

ድጋፉን በማሰባሰብ ሂደቱ ውስጥ በአሜሪካ የሚገኘው ግብረ ሠናይ ድርጅት ኤሬ አፍሪካም ይገኝበታል፡፡ ድጋፉን ለማዳረስ የተፈለገው 3 እስከ 18 ዓመት ውስጥ ላሉ ሕፃናት ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com