“ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ነው” – የተመ

Views: 121
  • ተፈናቃዮች አሁንም በሥጋት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል

በኦሮሚያና በቤንሻልጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ፣ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ አካባቢ የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያርጉ ድርጅቶች ከአጋር ተቋማት ጋር በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ነው በተቋሙ የተገለጸው፡፡

ከግንቦት 2011 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2011 ዓ.ም መንግሥት በሺዎች የሚቆጠሩ በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ አካባቢ የሚኖሩ እና ከቤንሻልጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ካማሺ እና አሶሳ ዞኖች እንዲመለሱ ድጋፍ አድርጓል ተብሏል፡፡

ነገር ግን፣ ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ የሚኖሩበት አካባቢያቸው ተመልሰዋል ብሎ መደምደም እንደማይቻልም እየታዩ ያሉ ሁኔታዎች ይጠቁማሉ ሲል ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግለጫ ያብራራው፡፡

ከምዕራብ ወለጋ ወደ ካማሺ ዞን መንግሥትና አጋር ድርጅቶች ድጋፍ አድርገውላቸው፤ በአካባቢው ያለውን ፀጥታ ደግሞ የመከላከያ ኃይል በቁጥጥር ስር አውየዋለሁ ካለ በኋላ እንኳን፣ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መመለስ አለመፈለጋቸውን የጠቆመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው፡፡

በነጆ ከተማ ያሉት ተፈናቃዮች እንደሚሉት ወደ ቤንሻልጉል ጉሙዝ ክልል ከተመለስን በኋላ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዳናገኝ ተከልክለና ብለዋል፡፡

እነዚህ ተፈናቃዮች አሁን ያሉበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ሲሆን፣ በተለይም ሴቶችና ህፃናት በአንድ ቤት ውስጥ በብዛት ተከማችተው እየኖሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የመጠለያ ቦታዎች በብዛት አለመኖር ችግር ከአየር ንብረቱ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ እንግልት እየገጠማቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአጋር ድርጅቶች ወደ አካባቢው ገብተው ድጋፍ እንዳያደርጉ አሁን ያለው ዝናባማ ወቅትና በአካባቢው ያለው የመኪና መንገድ ምቹ አለመሆን ለድጋፍ አሰጣጡ አስቸጋሪ ሁኔታን እንደፈጠረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ተፈናቃዮቹ በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ሁኔታን ማሻሻል፤ ሰላምን ማጠናከርና እርቅን ማውረድ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ይህን ለማድረግም የራሳቸውን ጥረት እንደሚያደርጉም ተናረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com