ካፍ በኢትዮጵያ የሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች ከደረጃ በታች ናቸው አለ

Views: 149

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ኢትዮጵያ አህጉራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ጨዋታዎችን ለማድረግ  የእግር ኳስ ሜዳዎቿ  ከደረጃ በታች ናቸው ሲል በቅርቡ መረጃ አውጥቷል፡፡

ካፍ ኢትዮጵያ የ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታደርግ እድል ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ሀገሪቷ ውድድሩን ማዘጋጀት የምትችልበትን አቋም ለማወቅ ካፍ በስራ አስፈፃሚዎቹ በኩል ሜዳዎቹ አሰሳ እንዲደረግባቸው አስደርጓል፡፡

የካፍ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም ሁለት ጊዜ ባደረጉት አሰሳ ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት ዝግጁ አይደለችም የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ዕድሉን ለካሜሮን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እንዳሉት ካፍ የአዲስ አበባ ስታዲየም የከፋ ችግር እንዳለበት ገልፆልናል፤ ነገር ግን፣ የባህር ዳር እና የመቀሌ ዓለም አቀፍ ሜዳዎችን ዝግጁ በማድረግ ጨዋታዎች እንዲካሄዱባቸው እያደረግነው ነው ብለዋል፡፡ በካፍ ውሰኔ መሠረት ውርደት ውስጥ ገብተናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽንን ጨምሮ የየክልል ኮሚሽኖች በትኩረት እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

ካፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ችግሮቹን ፈትቶ በቅርቡ ሪፖርት ካላደረገ ውድድሮችን ወደ ጎረቤት አገራት እናዘዋውራለን ባለው መሠረት ችግሮቹን በአፋጣኝ ፈትቶ ዝግጁ ለማድረግ ፌደሬሽኑ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግም አስታውቋል ሲል የዘገበው ዐማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው::

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com