የቻይናው ተቋራጭ ሸገርን በማስዋብም አሻራ ማሳረፍ ጀመረ

Views: 163

ሀብቴ ታደሰ እና እየሩስ ተስፋዬ

በኢትዮጵያ በበርካታ ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመያዝ ቀዳሚ የሆነው የቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ /ሲሲሲሲ/ የወንዞች ተፋሰስ ወይም “ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት የመጀመሪያው ዙር 12 ኪሎ ሜትር እና 48 ሄክታሩን ፕሮጀክት መገንባት ጀመረ፡፡

የቻይናው ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) ከዚህ በፊት  የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ግንባታን የሰራ ተቋራጭ ሲሆን፣ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የመቀሌ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጄክትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቀው የአዲስ አበባ የወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ልማት (ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት) የመጀመሪያው ምዕራፍ  ግንባታ ተረክቦ በይፋ ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የፕሮጀክቱ ዲዛይን እና የአፈር ጥናቱ ስራ መጠናቀቁ የታወቀ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍም በሚቀጥለው ዓመት ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሰባት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀገራችን ታላቅ የኮንስራክሽን ግንባዎችን እያከናወነ የሚገኘው የቻይናው ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) የሀገራችንን ዋና ከተማ አዲስ አበባን የማዋስብ ስራም ተሳታፊም መሆን ችሏል፡፡

ይህ ኩባንያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሌሎች በርካታ የግል እና የመንግሥት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገነባውን አዲሱን የዓባይ ድልድይን ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በቅርቡ መስማማቱ ይታወቃል፡፡ በሌላም በኩል፣ በቦሌ መንገድ የቻይናው ተቋራጭ በ1,435 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፈውን 23 ወለል ሕንፃ ለመገንባት ጨረታውን አሸንፎ በ812 ሚሊዮን ብር እየገነባ ይገኛል፡፡

የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የመጀመሪያው ክፍል ፕሮጀክት፣ ከዚህ በፊት “የሸራተን ማስፋፊያ” በሚል የሚታወቀው ቦታ ላይ ያለው ሲሆን፣ ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ለፕሮጀክቱ ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ከውጭ አገር በመግባት ላይ ከመሆናቸውም በላይ፣ ግንባታው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የፅዳት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

“ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ያለውና “ሴንተራል ፕላዛ” የሚል ስያሜ መጀመሪያ የተሰጠውን  ለቫርኔሮ ሥራ ተቋራጭ የነበረ ቢሆንም፣ የቻይና መንግሥት በነፃ እሰራለው በማለቱ ከቫርኔሮ ተነጥቆ በቻይና ኩባንያ ሥራው ተጀምሯል፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም፣ ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት በሦስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዋና ከተማዋ ውስጥ በብዛት የተበከሉ ወንዞችን እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን፣ በተከታታይ እነዚህን ወንዞች የማጽዳት ብሎም የወንዝ ዳርቻዎችን የማስዋብ ሥራዎችም እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡

ከአምስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ይኖሩባታል የተባለቸውን አዲስ አበባን ለማስዋብም እና ከባቢያዊ አየሯንም ምቹ ለማድረግ ሃሳቡን የጠነሰሱት ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት የወንዞች ተፋሰስ ሥራም ከእንጦጦ ጀምሮ እስከ አቃቂ ድረስ  እንደሆነ  መገለፁ ይታወሳል፡፡

ፕሮጀክቱ በተጨማሪም የመናፈሻ ቦታዎች፣ የብስክሌት መንገዶች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ ችግኞች የሚተከሉባቸው ቦታዎች ያሉት ሲሆን፣ የከተማ ግብርና ልማት ያካተተ ነውም ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com