በሕገ-ወጥ ዝውውር ከ880 በላይ ተሳትፈዋል

Views: 139

በዐማራ ክልል የሕገ ወጥ ዝውውርን ለመግታት በተጠናቀቀው የ2011 በጀት 882 ግለሰቦችን በሕገወጥ የሰዎች ዘውውር መሳፋቸው ታውቋል፡፡

የዐማራ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ከተያዙት ግለሰቦች በተጨማሪ፣ ሌሎች ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 32 ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት መቅረባቸውም ታውቋል፡፡

በተጠናቀቀው የ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት ከተያዙት 882 ኢትዮጵያውያን መካከል 440 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ የተቀሩት ወንዶች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር  እየጨመረ የመጣው ከኢኮኖሚ ጋር  የተያያዘ ችግር  እንደሆነ እና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፣ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ውጭ አገር ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ እንደሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም መዳረሻቸውን የዐረብ ባህረ ሰላጤ ሀገራት፣ አውሮፓ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com