ስለ ሥነ-ምኅዳራችን የሣምንቱ አንዳንድ ነጥቦች

Views: 115
  1. ኢትዮጵያችግኝ በመትከል የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

ዛፎች ለሥነ-ምህዳራችን በጣም አስፈላጊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የሚፈጠርን የ‹‹ግሪን-ሃውስ›› ልቀትን ተፅእኖ ሚዛን ለመጠበቅ እገዛ አላቸው፡፡

በመሆኑም፣  ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በችግኝ ተከላ የዓለምን ክብረወሰን ማስመዝገቧ ጥቅሙ ከሀገር አልፎ ዓለማቀፋዊም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በ12 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 350 ሚሊዮን ችግኞችን ተክሏል ሲልም eco-warrior princess በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

ይህም፣  የአየር ንብረት ለውጥ እና የዓለም ሙቀት መጨመር ለመዋጋት በመላው አገሪቱ የደን ልማትን ለማስፋፋት ‹‹የችግኝ ተከላ›› የፕሮጀክቱ አንድ አካል ነው፡፡

2 በህንድ የነብሮች ቁጥር መጨመር

በዚህ ሳምንት ለአለማችን አየር ንብረት ለውጥ ጥሩ ዜና ከተባሉት ውስጥ በሁለተኛነት የተቀመጠው በህንድ አገር የነብር ቁጥር በ30 በመቶ መጨመሩን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስታውቀዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2014 ዓ.ም ቁጥራቸው ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስድት ነብሮች ሲኖሩ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ቁጥራቸው ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሰባት መድረሱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸው፤ ህንድ በአሁን ወቅት ከባቢያዊ አየሯ ምቹ እየሆነ በመጣቱ ነው፤ ይህ ሊሆን የቻለው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

3 ፔፕሲ እና ኮካኮላ የፕላስቲክ ምርታቸው ላይ ማሻሻያ ሊያደርጉ ነው

ሁለቱ ግዙፍ የለስላሳ መመጥ አቅራቢ ኩባንያዎች፣ ከጥቂት ቀናት በፊት የፕላስቲክ ምርቶቻቸው ላይ ማሻሻያ እንደሚያርጉ በማስታወቅ፣ ለአየር ንብረት የተሻለ አማራጭ ነው የሚሉትንም ሃሳብ ማምጣታቸውንም ይህ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

በመሆኑም፣ ኮካ ኮላ የፕላስቲክ ምርቶቹ 50 በመቶ መልሶ ጥቅም ላይ ሊውል በሚችል መልኩ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለማምረት ቁርጠኛ ነኝ ሲል አስታውቋል፡፡

ፔፕሲም በበኩሉ፤ ምርቶቹ አካባቢን በማይበክሉ መልኩ በአሉሙኒየም የተሰሩ ለማድረግ አስበዋል፡፡ ይህም፣ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ወደ ተግባር እንገባለን ብሏል፡፡

4 ፓናማ የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አግዳለች

ሀገሪቱ በሱፐርማርኬቶች፣ በመድኃኒት ቤቶች እና በሌሎች የመገበያያ ቦታዎች የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገዷ ተሰምቷል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶችን በማገድ ፓናማ ከመካከለኛው አሜሪካ አገራት ቀዳሚዋ ስትሆን፣ እስካሁንም ከ90 በላይ አገራት የፕላስቲክ ከረጢቶችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገዳቸውም ይታወቃል፡፡

5. የዓለማችን ትልቁ ሆቴልም የፕላስቲክ ምርቶችን አግዷል

የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴሎች ቡድን (IHG) የፕላስቲክ ምርቶችን ለአየር ንበረት ለውጥ አደገኛ በመሆናቸው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገዱ የሳምንቱ መልካም ዜና ነው ተብሏል፡፡

በተለይም፣ የሳሙና ማስቀመጫ እና ሌሎች ጥቃቅን የሚመስሉ ግን አየርን በመበከል አደገኛ የሆኑ የፕላስቲክ ምርቶችን ላለመጠቀም አግዷል፡፡

ሆቴሉ እስካሁን 200 ሚሊዮን የፕላስቲክ ጠርሙሶች ማስወገዱን አአስታውቀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com