በሺዎች የሚቆጠሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ

Views: 114

በሺዎች የሚቆጠሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች፣ በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገራቸው መመለስ መጀመራቸው ተነገረ፡፡

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት፣ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዳይኖር ባደረገው ጥረት መሠረት፣ በርካቶች ባለፈው በጀት ዓመት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል በማለት የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነው፡፡

ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከአስራ ሁለት አገራት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተብሏል፡፡

በባለፈው በጀት ዓመት፣ ከሃያ አራት ሺህ በላይ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በአስራ ዘጠኝ አገራት የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ውጭ አገራት በአስከፊ ሁኔታ የሚኖሩ ዜጎቿን ከለላ በመስጠትና ከመንግሥታቱ ጋር በመደራደር ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ አድርጋለች፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com