በጅማ በጀልባ አደጋ አምስት ሰዎች የት እንደገቡ አልታወቀም

Views: 127

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ኃይቅ ላይ፣ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ባሕላዊ ጀልባ ሰጥማ አምስት ሰዎች የት እንደገቡ አለመታወቁን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ፣ አደጋው ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 5 ስዓት ከ30 ደቂቃ አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎች ተሳፍረው ሲጓዙ አደጋው መከሰቱ ተነግሯል፡፡

በወረዳው አስተዳደር አካላት፣ በአካባቢው ነዋሪዎች እና በጠላቂ ዋናተኞች አማካይነት የ13 ሰዎች ሕይወት እንደተረፈም ተገልጿል፡፡

የቀሪዎቹ አምስት ሰዎች ፍለጋ የቀጠለ ሲሆን፣ የጀልባዋ ቀዛፊ ግን በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ፣ በሚያዚያ ወር በዐማራ ክልል የሚገኘው ጣና ኃይቅ ላይ አንዲት ጀልባ ሰጥማ 12 ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን፣ ፖሊስም ለአደጋው መንስዔ ጀልባዋ ከአቅሟ በላይ ሰዎችን በመጫኗ ነው ማለቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com