ዜና

ኢትዮጵያ በማዕድን የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ

Views: 364

ኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት ዓመት፣ በማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ገቢ በስድስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዷን ይፋ አደረገች፡፡

ይህን ትልቅ ዕቅድ ለማሳካት፣ ሀገሪቷ የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ማቋቋሟን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በብሔራዊ ኮሚቴው አባልነት የተውጣጡት የተለያዩ ኢትዮጵያውያ ሚኒስትሮች ሲሆኑ፣ አባላቱ ዘርፉን የሚያሻሽሉ እና ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኛቸውን ጥቅማ-ጥቅሞች ለማሳደግ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን ለማደስ የሚሰሩ ናቸው ተብሏል፡፡

በተጠናቀቀው የ 2011 ዓ.ም በጀት ዓመት፣ ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ገቢ እንዳገኘች፣ የኮሚቴው ሊቀመንበር አቶ ይድነቃቸው ተሰራ ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ ያለው የሕግ ማዕቀፍ ክፍተት፣ በባለድርሻ አካላት መካከል ውህደት አለመኖር፣ ማዕድንን በሕገ-ወጥ መንገድ ማውጣት እና በኮንትሮባንድ ማጓጓዝ በሀገሪቱ ያለውን የማእድን ዘርፍ በአሉታዊ መልኩ እየጎዳው ነው ተብሏል፡፡

የኮሚቴው ሊቀመንበር አቶ ይድነቃቸው እንዳሉት፣ ኮሚቴው አሁን በተገኙት የማዕድን ዘርፉ ችግሮች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ያሉ ሲሆን፤ እነዚህ ችግሮች በዘርፉ በቂ የሆነ መመሪያ ያለመኖር እና የኮንትሮባንድ ሥራ መስፋፋት ናቸው ብለዋል፡፡

በቀጣይ ኮሚቴው ከባለድርሻ አካላት ጋር፣ ከጉምሩክ ጽ/ቤቶች፣ ከደህንነት እና ሌሎች አካላት ጋር በመሆን፣ የማዕድን ዘርፍ አምራቾችን እና ላኪዎችን በማበረታታት ዘርፉን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com