ኢትዮጵያዊያን ዝነኞች በአትላንታ ተሸለሙ

Views: 161

ዘንድሮ በአሜሪካ ግዛት አትላንታ የተዘጋጀው የሠሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታን አስመልክቶ ለመጀመሪያ ግዜ በሥደት የሚገኙት ጋዜጠኞች ያደረጉት የእዉቆቻችንን እናክብር በሚል መፈክር ታላላቅ ሠዎችን ለሽልማት በማቅረብ ፥

በጋዜጠኝነት ዘርፍ – ሄኖክ ዓለማየሁ

በህትመት ዘርፍ – ኤልያስ ወንድሙ

በሥነ ጽሑፍና ሥነ ግጥም ዘርፍ – በእዉቀቱ ሥዩም

በቴአትር ዘርፍ – ዓለምጸሐይ ወዳጆ

እንዲሁም በሙዚቃው ዘርፍ ተወዳጁንና በትላንትናዉ ዕለት 43ተኛ ዓመት የልደት በዐሉን ያከበረዉን ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ሽልማት ተበርክቶለታል ።

በነገራችን ላይ ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በዛሬዉ ዕለት እዛው አሜሪካ አገር ዋሽንግተን ዲሲ ከአፍሪካ ህብረት ማህበር ልዩ ሽልማት ይበረከትለታል ።

Via – ጌጡ ተመስገን

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com