በኮንጎ ምሥራቃዊ ግዛት ኢቦላ ተከሠተ

Views: 155

ቫይረሡ በአካባቢው ሊከሠት የቻለዉ አንድ ታማሚን ጨምሮ 18 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በትናንትናው ዕለት ጠዋት ላይ ከቡተምቦ ተነስቶ ኖርድ ኪቩ ግዛት ዉስጥ ወደምትገኘዉ ጎማ ከተማ መግባቱን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል ።

በዚህም ግለሰቡ ላይ በአፋጣኝ በተደረገ ምርመራ የኢቦላ ቫይረስ እንዳለበት የተረጋገጠ ሲሆን ፥ ከታማሚዉ ጋር የተሳፈሩ መንገደኞች እና አሽከርካሪው ክትባት እንዲሰጣቸው መደረጉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታዉቋል ።

ጎማ ከተማ በሀገሪቱ በዓመቱ በሁለተኛ ደረጃ ቫይረሱ ሥርጭት ከተመዘገበበት አካባቢ በስተደቡብ አቅጣጫ የምትገኝ ሠፊ ከተማ መሆኗም ነዉ የተነገረዉ ።

Via – FBC

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com