ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የ 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሥምምነት ተፈራረሙ

Views: 170

የመግባቢያ ስምምነቱን የኤፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በተባበሩት ዐረብ ኤሚሬቶች በኩል የከሊፋ ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ ሁሴን ጃዚም አል ኖዌስ ተፈራርመዉታል ።

ድጋፉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የሚዉል ነዉ ተብሏል ።

ከዚህ ባለፈም ለቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሥራዎችን ለመደገፍ ይዉላል መባሉንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል ።

Via – FBC

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com