ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ካታር ገብተዋል

Views: 282

የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው እና አስፈላጊውን መሥፈርት ያሟሉ ኢትዮጵያዉን ሠራተኞች በዛሬዉ ዕለት የካታር መዲና ዶሀ ደርሰዋል ። ባለፈዉ ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ ዐረቢያ ፣ ካታር እና ዮርዳኖስ ጋር የሥራ ሥምምነት የተፈራረመ ቢሆንም፤ ሥምምነቱ ተግባራዊ ሳይሆን ረዥም ግዜ ቆይቷል ።

” ምንም እንኳ ዛሬ ዶሀ የገቡት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ 10 ባይበልጥም በሺህ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን ሠራተኞች መንገዱ መከፈቱን ማብሰሪያ ይሆናል ” ይላል የዶቼቬሌዉ የሳዑዲ ዐረቢያዉ ወኪል ነብዩ ሲራክ ።

ወደ ዉጭ አገራት የሚደረግ የሥራ ስምሪት ከ 2008 ዓ.ም ጀምሮ ታግዶ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አዲሱ የዉጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ 923/2008 በይፋ መጀመሩ በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን መብት ፣ ክብርና ጥቅም የሚያስከብር ነዉ ተብሎ ይታመናል ።

Via – DW ዐማርኛ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com