ዜና

ከሳዑዲ ዐረቢያ ድንበር የድረሱልን ጥሪ

Views: 359

ሳዑዲ ዐረቢያ ድንበር የሚገኙ እሥረኞች ድረሱልን እያሉ ነዉ ። ቁጥራቸዉ ከ 500 በላይ የሚሆኑና በየመንና ሳዑዲ ዐረቢያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ እሥር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዊያን አቤቱታችን ለመንግሥት ንገሩልን ሲሉ ገለፁ ። በህክምና እጦት እየተሠቃየን ነዉ ያሉት ኢትዮጽያዉያኑ እሥረኞች በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥያቄ የተቀነሰልን የእሥር ግዜ ተግባራዊ አልሆነምም ብለዋል ።

ሳዑዲ ዐረቢያ የሚገኘዉም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊያሠጠን ይችል ነበር ሲሉም ነዉ የተናገሩት ።

Via – DW ዐማርኛ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com