በቤኒሻንጉል ክልል የተከሠተዉ ጥፋት

Views: 283

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ በፀጥታ ችግር ቀያቸዉን ትተዉ የሄዱ ሠዎችን ንብረት የፀጥታ አካላት ሲዘርፉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸዉ ተሠምቷል ።

በክልሉ ማንዱራ ወረዳ ገነተ ማርያም ቀበሌና አካባቢዉ ከሠሞኑ የጸታ ችግር ተፈጥሯል ። በዚህም በቀስት እና በጥይት በታገዘ ጥቃት የሠዎች ህይወት አልፏል ፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል ። ለዘመናት በሠላም እና ኢትዮጵያውያን መካከል ጥርጣሬ እና ጥላቻ እንዲፈጠር በመደረጉም የፀጥታ ችግሩ ከመሻሻል ይልቅ ስጋቶች እየጨመሩ እንደሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል ።

በምዕራብ ዕዝ 24ቸኛ ክፍለ ጦር ፣ ሻለቃ ሦስት ፣ የ1ኛ ሻምበል አዛዥ ምክትል መቶ አለቃ መሐመድ ጀማል በአካባቢው ለማረጋጋት ሥራ መሥራታቸውን ገልጸዋል ። ችግሩ የተከሠተው የተደራጁ ቡድኖች በሥድስት ቀበሌዎች ተደራጅተው በሠላማዊ ነዋሪዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ በመጀመራቸው እንደሆነ ምክትል መቶ አለቃው ለአብመድ ተናግረዋል ። በዚህም የሠዎች ህይወት ማለፉንና የዐካል ጉዳትም መድረሱን አረጋግጠዋል ።

ከጸጥታ ችግሩ በስተጀርባ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃዎች የሚገኙ የክልሉ ሠዎች አሉበት ብለዉ እንደሚያምኑም አዛዡ ገልጸዋል ። ከቀበሌ እስከ ክልል ያሉ መሪዎች ለማረጋጋት ሥራው እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ሁኔታውን ለማረጋጋትም ሆነ ለመተባበር ቀና ምላሽ አለመስጠታቸውንም ነዉ በማሳያነት የተናገሩት ።

Via – አብመድ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com