ሙዚቀኛው ለትግራይ ሕዝቦች ፩ እንሁን ሲል ጥሪውን በዜማ አቀረበ

Views: 432

የሬጌ ስትል አቀንቃኙ ሰለሞን ይኩኖአምላክ፣ ለትግራይ ተወላጆች ሁሉ አሁን በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ውጥረት ምክንያት በማድረግ፣ የአንድነት ጥሪውን ጊታሩን በመጫወት፣ ግጥም እና ዜማው በማዋሃድ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በቀላሉ ታዋቂ እና ተቀባይነትን ለማግኘት የፍቅር ሙዚቃዎችን ማዜም ይቻላል፤ አሁን ግን ለትግርኛ አድማጮች መስራት የሚያስፈልገው አንድ የሚያደርገን ሙዚቃዎችን ማዜም ብቻ ነው የሚል አቋም አለው- ድምፃዊው፡፡

ሙዚቀኛው ‹‹እድሜ ለ42 ዓመቱ ዐብይ አህመድ የትግራይ ሕዝብ በዘረኝነት ሳቢያ እንዲገፋ አድርጓል›› ይላል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሰው አክቲቪስት እና ፖለቲከኛ እንደሆነም ለኤኤፍፒ አብራርቷል፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡

መንግሥት ‹‹መፈንቅለ መንግሥት ነው›› ባለው ጉዳይ፣ ጥቃቱ ያነጣጠረውና አምስቱ ሕይወታቸው ያለፈው ተጎጂዎች የዐማራ እና የትግራይ ክልል ተወላጆች ናቸው ብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቤተ-መንግሥት ከገቡ በኋላም ‹‹ብዙ የትግራይ ሕዝቦች ለረሃብ ተጋልጠዋል›› ሲልም አስረድቷል፡፡

የመቀሌ ዩኒቨርስቲው መምህር የሆኑት ነብዩ ስህለ ሚካኤል ደግሞ ትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደሆነ እና በፖለቲካው፣ በእግር ኳሱ ጋር በተያያዘም ያለ አግበብ እየተፈረጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com