ዜና

መንግሥት የጀመረውን የምሕረት ተግባር እንዲቀጥል ታራሚዎች ጠየቁ

Views: 290

– “የሃይማኖት ተቋማትም ለበዓል ጊዜ ብቻ አትፈልጉን” ብለዋል

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች፣ መንግሥት የጀመረውን የምሕረት ተግባር እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የተለያዩ ወንጀሎችን ፈጽመዋል ተብለው በሕግ የተፈረደባቸው ግለሰቦች፣ የእስር ጊዜያቸውን በማረሚያ ቤት እያሰለፉ መሆኑን የሚገልጹት ታራሚዎች፣ መንግሥት ይህንን ጉዳይ አጥንቶ ምሕረት ለሚገባው- ምሕረት እንዲሰጠን እንፈልጋን ሲሉ ዓርብ ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹በመጽሐፍ እንታረም›› በሚል መሪ ቃል በተሰናዳው መርሃ-ግብር ላይ ተናግረዋል፡፡

ምሕረት የሚደረግላቸው የወንጀል ዓይነቶች እንዳሉ እናውቃለን የሚሉት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሕግ ታራሚዎች፣ ይህንን አውቀን ከመንግሥት በኩል ምሕረት እንዲደረግልን እንፈልጋን ሲሉም በቦታው ለተገኘችው ዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ታራሚዎቹ በመርሃ-ግብሩ ላይ ለተሳተፉ የሃይማት ተቋማት መሪዎች፣ ‹‹ለበዓላት ቀን ብቻ አትፈልጉን፤ የሃይማኖት አባቶች ናችሁና በሌላም ቀናት ቢሆን አስታውሳችሁን ጠይቁን፤ እባካችሁ አስታዋሽ የለንም›› ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com