የንባብ ሳምንት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተካሔደ ነው

Views: 407

ዓርብ ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም፡- የሕግ ታራሚዎችን የንባብ ባሕል ለማሳደግ “በመጻሕፍት እንታረም” በሚል መሪ ቃል በአሁኑ ጊዜ ዝግጅቱ እየተካሄደ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ሕይወታቸውን በማረሚያ ቤት ያሳለፋ የቀድሞ ባለስልጣናትም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመገኘት ለታራሚዎች ምክራቸውን ለግሠዋል::

የቀድሞ የደርግ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩ ኮ/ል ፍሥሃ ደስታ 20 ዓመት በእስር ማሳለፋቸውን በመግልጽ ታራሚዎች ጊዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ አሳስበዋል::

“አብዮቱ እና ትዝታዬ”ን መጽሐፍ የጻፍኩት ማረሚያ ቤት ነው ያሉት ኮ/ል ፍሥሃ ደስታ፤ ጊዜያችሁን በንባብ ብቻ ሳይሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እና እቅድ በማውጣት የእርምት ጊዜያቸውን እንዲያሳልፋም ምክራቸውን እና ልምዳቸውን አካፍለዋል::

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com