ዜና

በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት መጠናከር አለበት ተባለ

Views: 331

ኢትዮጵያና ኬኒያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ሲሉ የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ሲያደርጉ ቢታዩም፣ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ግን ግንኙኘታቸውን አጠናክረው መስራት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡

የኬኒያ የውጭ ጉዳይ አስተዳደር ዋና ፀሐፊ አባቡ ናምዋምባ ከአትዮጵያ ጋር ከታሪፍ ነጻ የንግድ ግንኙነት እንዲኖር የንግድ ስምምነቶች እንደተፈራረሙ የገለፁ ሲሆን፣ ለዚህ ውጤታማነት ግን የአገራቱ የተንዛዛ የመንግስት አሰራር (ቢሮክራሲ)፤ የንግድ እገዳና ማዕቀብ ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ-ኬንያ ግንኙነት የመታሰቢያ 55 ዓመት ዝግጅት በናይሮቢ በተካሄደበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2012 ሁለቱ አገራት የኢኮኖሚ ጥምረት ለመመስረት መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ስምምነቱም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት፣ በምግብ ዋስትና እና ዘላቂ ኑሮን የተሻለ ለማድረግ ለመስራት ከስምምነት ደርሰው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ እና ኬኒያም ‹‹ጆይንት ሚኒስትሪያል ኮሚሽን›› (ጄኤምሲ) በሚል መጠሪያ ስም የተሰየው የሁለቱ አገራት ስምምነት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመስራት መስማማተቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መለሰ ዓለም በበኩላቸው፣ ሁለቱ አገራት የ55 ዓመት ግንኙነት እንዳለቸው በመግለፅ እኛ ባላንጣዎች አይደለንም፤ ይልቁንም ተፎካካሪዎች እንጂ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ኬንያ እና ኢትዮጵያ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ያላቸው አገራት መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ መለስ ዓለም፣ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን በማህራዊ ጉዳይ መጠናከር እንደሚኖርበት አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ አሁን ያለውን ለውጥ እና የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ለማዘዋወር እየተሰራ መሆኑ፣ በኬንያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ግንኙነት መጠናከር የራሱ ደርሻ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ትስስርን ያጠክራል የተባለው ‹‹የላሙ ወደብ›› ፕሮጀክት ሥራውም በቅርብ እንደሚጀመር የኬኒያ ውጭ ጉዳይ አስተዳዳዳሪ ዋና ፀሐፊ ገልፀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com