በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ማህበር ሊመሰረት ነው

Views: 506

በሰሜን አሜሪካ የሥነ-ጽሑፍ፣ ቴአትር፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ሥዕል፣ ቅርፃ ቅርፅ እና ሌሎች መሰል ሙያ ያላቸው በርካት ኢትየጵያውን ይኖራሉ፤ ይህንን ምክንያት በማድረግ እና እነዚህን የጥበብ ሰዎች እንዲሁም አድናቂዎች በአንድ ለማሰበሰብ እና ለማደራጀት ‹‹በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ማህበር›› የተሰኘ ተቋም ሊመሰረት ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ተነግሯል፡፡

በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ውስጥ ነዋሪ በሆነው እንዲሁም በስነግጥሞቹ እና በሥነ-ጽሑፍ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ታዋቂነትን ባተረፈው በቴዮድሮስ ታደሰ ሃሳብ አፍላቂነት ይቋቋማል የተባለው ማህበር ተግባራዊ ሊሆን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል ተብሏል፡፡

አንጋፋዋ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆን ጨምሮ በጸሐፊ ቴዮድሮስ ታደሰ አነሳሽነት በቅርቡ አስራ አምስት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የፊታችን ሃሙስ 27 ቀን ወይም (ጁላይ 04) በአትላንታ ጆርጅያ ላይ ለማደራጀትና ተቋም ሊመሰርቱ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ገልፀዋል፡፡

ፀሐፊው ቴዮድሮስ ታደሰ ማህበሩን መመስረት ያስፈለገው በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ የኪነ-ጥበብ ሰዎች መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር፤ እርስ በርስ ጠንካራ የግንኙነት መስመር ለመመስረት እና የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ጥብብ በመጠቀም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በበጎ ስራ ላይ ለመተባበር ነው ብሏል፡፡

በተጨማሪም በየአመቱ የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚዘጋጅባቸው ከተሞች ላይ በመገኘት ለታዳሚው ጥሩና የተሻለ አማራጭ የሚፈጥር፤ ደረጃውንም የጠበቀ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ለማቅረብ ዓላማ ያለው እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምስረታውም ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም (04,2019) አትላንታ በሚገኘው Doubletree by Hilton ሆቴል ውስጥ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆን ጨምሮ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ አንጋፋ እና ተወዳጅ የጥበብ ሰዎች የሚካፈሉበት መርሃ- ግብር ተዘጋጅቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com