መሆን ከሚሸል ኦባማ መጽሐፍ የተወሰደ

Views: 310

• የፖለቲካ ልማድ ሆኖ አንዱ አንዱን ማብጠልጠል፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ የተለመደ ቢሆንም፣ ፖለቲካው ሲያልቅ መተቃቀፉ አሜሪካዊያኑን ከሚያኮራ የፖለቲካ ባህላቸው ውስጥ አንዱና ዋንኛው ነው፡፡

• ከልጅነት ጀምሮ ንግግር በማደርግበት ጊዜ የሰዎች ክብር ሳይነካ መጨረስ እንዳለብኝ የግል እምነቴ ነው፡፡ እንዲያውም እኔና ባራክ እንደ መመሪያችን ያደረግነው አንድ ታዋቂ ኃይለ ቃል ነው፡፡ “እነሱ ወደ ታች ሲወርዱ እኛ ወደ ላይ ከፍ እንላለን”

• የዚያን እለት ምርጫው በመላ አሜሪካ እየተከናወነ እያለ እኔና ባራክ ኋይት ሃውስ ውስጥ በሚገኘው የፊልም ማሳያ ውስጥ ፊልም እያየን ነበር፡፡ ያን እለት የማስበው ይህን ትልቅ ኃላፊነት ለቀጣይ ባለ ተራ አስረክበን መደበኛ ህይወታችን እንደምንመራ ነበር፡፡

• እኔና ባራክ መጪው ጊዜያችንን በስማችን ፋውንዴሽን ከፍተን በአዲሱ ትውልድ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊኖራቸው የሚችሉ መሪዎች ለማፍራት መስራት እንዳለብን ተነጋገርን፡፡

• ነገሮችን እንዳለ መቀበልና እውነታውን ማስተናገድ ጊዜው የሚጠይቀው ጥበብ ነው፡፡

• የመጀመሪያው በኋይት ሃውስ የኖረ ጥቁር ቤተሰብ እንደመሆናችን፣ ለእኛ ቤተሰብ ሌላው ትልቅ ድል ያለ ምንም የጎላ ቅሌት ከኋይት ሃውስ መውጣታችን ነው፡፡

• ያደኩት በብዙ መልኩ ድሀ ሊባል የሚችል ደቡባዊ ክፍል ውስጥና አባቴም የአካል ጉዳተኛ በመሆኑ፣ ለቤተሰቡ ወጪ መሸፈኛ የሚሆን በቂ ገንዘብ አልነበረንም፡፡ እንዲሁም ላለፉት አስር የሚጠጉ አመታት የአሜሪካን ጽንፍ እና መራር እውነታዎች እና ቁስል፣ እስከ ማገገሚያቸው አይቻቸዋለሁ፡፡ እንግዲህ አሜሪካንን የማያት እንዲዚህ ነው፡፡ እንዲም ሆኖ ታሪካችን በተነገሩበት ሁኔታ እወዳቸዋለሁ፡፡ አገሬንም አጥብቄ እወዳለሁ፡፡

• ኘሮፌሽናል ቅጥር ለመፈፀም እድል ካገኘሁበት ከሲዲኒ እና አስቴን የሕግ ድርጅት ጀምሮ እስከ ኋይት ሃውስ ድረስ ያስተዋልኩት አንድ ነገር ቢኖር በብዛት ነጮችና ወንዶች የተሻለ እድል ያላቸው መሆኑን ነው፡፡

• የባራክ ሚስት ሆኛለሁ፣ ሲጨምር የአሜሪካ ኘሬዘዳንት ሚስትም ነኝ! ነገር ግን ከአንድ ወንድ ጋር እንዴት በሰላምና በፍቅር አብሮ መኖር እንደሚቻል ተምሬ አልጨረስኩም!

• መሆን፤ ትእግስትን እና ጥልቅ ፍላጎት ይጠይቃል፡፡

• ብዙ ሰዎች የሚጠይቀኝ አንድ ጥያቄ አለ፡፡ ወደፊት በየትኛው የፖለቲካ ሥልጣን ፍላጎት እንዳለኝ፡፡ ሥልጣን ለማግኘት ፍላጎት የለኝም፡፡ ኖሮኝም አያውቅ! በሰማያዊ እና በቀይ የጽንፍ ሹክቻ በሚመራ እና የራስን ብቻ ይዞ የሌሎችን በመተቸት ጀብድ በሚሰራበት ፖለቲካ ንግድ ውስጥ መሳተፍ አልፈልግም፡፡

• ፖለቲካ ውስጥ ቅን ሀሳብ ቦታ የለውም፡፡

• አዲሱ ኘሬዜዳንት በሚያረጋቸው አወዛጋቢ እና ግራ አጋቢ ንግግሮች እና ስህተቶች በየቀኑ በአሜሪካዊያን መካከል ጥርጣሬ እና ፍርሀት ሲፈጥሩ ማየት እንቅልፍ ይነሳኛል፡፡

• ሁላችንም በሀገራችን ዲሞክራሲ ላይ የየራሳችን አስተዋጽኦ አለን ምርጫ ሁልግዜም የተሻለ አማራጭ ነውና፣ ይህ የፍርሀቴ ማርከሻ እና የእምነቴም ደግሞ መጀመሪያ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com