ጨጨብሳ – ለቁርስ እና ለመክሰስ

Views: 726

ሰላም- ሰላም፣ እንዴት ናችሁ ላጤዎች?

ዛሬ ልናሳያችሁ የወደድነው የምግብ አዘገጃጀት በጣም ቀላል እና ቶሎ ለቁርስ ወይም ለመክሰስ የሚደርስ ምግብ ነው፡፡ ጨጨብሳ ይባላል፡፡

በተለይ ለዝናባማ ቀን የሚሆን ምግብ ነው፡፡ በዓየር ንብረቱ ከሰውነታችን የሚነጠቀውን ሙቀት ያካክስልናል- ይላሉ የምግ ሳይንስ ባለሟሎች፡፡

ጨጨብሳ ለመስራት የሚስፈልጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
1.2 ሲኒ ፍርኖ ዱቄት
2.ቤኪኒግ ፓውደር
3.ጨው
4. ዘይት
5. በርበሬ
6. ማር ካለን፤ ከሌለንም ያለ ማር መስራት እንችላለን

አዘገጃጀቱ

በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ዱቄቱን እንጨምራለን፤ ቀጥለን ትንሽ ፔኪንግ ፓውደር እንጨምርና እናዋህደዋለን፡፡ እስኪቀጥን ድረስም ዱቄት ውስጥ ውሃ እየጨመርን እናዋህደዋለን፡፡

አዋህደን ከጨረስን በኋላ ያለው ስራችን ደግሞ መጥበሻችንን መጣድ ይሆናል፡፡
ከዛም ለቂጣ ያዘጋጀነውን ሊጥ ልክ እንደ እንጀራ በመጥበሻችን ላይ እንጋግረዋለን፡፡
እንዳያርብን እያየን የታችኛው የቂጣ ክፍል መብሰሉን እናይና ባልበሰለው በኩል እንገለብጠዋለን፤ ያልበሰለው ክፍል ሲበስል ደግሞ ቂጣውን እናወርደዋለን፡፡

የጨጨብሳው ሊጥ ከተረፈን አልያም ሌላ ጭማሪ ከፈለግን ደግሞ ልክ ከላይ እንደገለጽነው ደግመን መስራት እንችላለን፡፡

ይህን ካደረግን በኋላ የጋገርነውን ቂጣ ከፈለግን በቢለዋ በአራት መዓዘን ቅርጽ እያረግን ቂጣውን በመካከለኛ መጠን መቁረጥ፤ ከፈለግን ደግሞ በፈለግነው መጠን በእጃችን እንቆራርሰዋለን፡፡

ትልቁ ስራችንን ጨረስን፤ አሁን ደግሞ በጎድጓዳ ሰሃናችን ውስጥ 1 ማንኪያ በርበሬና ትንሽ ዘይት ወይም ቅቤ (እንደ ፍላጎታችንና ምርጫችን) ጨምረን የቆራረስነውን ቂጣ ጨምረን ማዋሃድ ይኖርብናል፡፡ ብዙ ጊዜ ማርና ቅቤ በአንድ ላይ አይመከርም፤ አንዱ ካለ በቂ ነው፡፡ ለጣዕም ሲባል!

በመቀጠል ደግሞ ለአንድ ወይም ለ2 ደቂቃ በመጥበሻችን ላይ እናደርገውና እንጥደዋለን ከዛም ማውረድ፡፡

አሁንማ የቀረን በዝርግ ሰሃ ጨጨብሳችን አድርገን በላዩ ላይ ደግሞ ማር ጨምሮ መብላት ብቻ ነው፡፡

መልካም ምግብ፤ ታዲያ በሚቀጥለው ወዳጅዎን መጋበዝዎትን አይዘንጉት!!!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com