ከሃሳብ መንደር

Views: 394

የሰው ልጅ ከእንስሳት የሚለየው በዋናነት በማሰቡ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ማሰቡም ሰው ከመሆኑ የመጣ እንደሆነ ደግሞ የፈጣሪን ህልውና የሚቀበሉትም ሆኑ የማይቀበሉቱ ሰዎች ሁሉ- በእውነታው ይስማማሉ፡፡

ስለዚህ፣ የሰው ልጅ በፍጥረቱ እንዲያስብ እና ለችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንዲያበጅ ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡ እኛም፣ ማሰብን እናበረታታለን፤ እናከብራለን፤ እናደንቃለን፤ እድንቀንም ሳንቀር፣ ከሃሳብ መንደር የጨለፍነውን በረከት እነሆ- እንላለን፡፡

እነሆ በረከት -፩-

 ዲዮጋን

 • ዲዮጋንን በባርነት የገዛውን ዜናዬዴስም መጥተህ ትእዛዝ መቀበልን ተማር ቢለው ዜናይዴስም ወራጅ ውሀ ተመልሶ የሚፈሰው ወደ ምንጩ ነው አለው፡፡ ይህን ጊዜ ዲዮጋን፣ በጠና በታመምክ ሰዓት የገዛኸው ባሪያ ሀኪም መሆኑን ብታውቅ የእሱን እርዳታ አትሻምን? አንዳንዴ ፏፏቴም ወደ ምንጩ ይመለሳል እኮ አለው!
 • አንድ ቀን ምግብን ለመመገብ የተመቸ ሰዓት የቱ እንደሆነ ተጠይቆ ሀብታም ከሆንክ ስትፈልግ ደሀ ከሆንክ ስትችል ለመመገብ ጥሩ ሰዓት ነው ብሏል፡፡
 • ታላቁ እስክንድር በቤተ መንግስት ክብር እንደሰጠው ወዳጁ ከአቴንስ ለዲዮጋን ሲነግረው ታላቁ እስክንድር ሲርበውና ሲጠማው እየጠበቁ አብሮ ከመብላትና ከመጠጣት በላይ ውርደት ከየት ታመጣላችሁ ብሏቸዋል፡፡
 • ዲዮጋን በህይወቱ የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ሽማግሌ ማየት ነው፡፡ ምነው? ቢሉት ወደ ኋላ እንጂ ወደ ፊት የሚያስበው የለውምና ብሏል፡፡
 • አንድ ቀን ዲዮጋን አንድ በፍልስፍና ትምህርት ጥናት የተጠመደ አቴናዊ ወጣትን ተመልክቶ ጥሩ እያደረክ ነው፡፡ የገላ ውበትን ከማድነቅ ወደ ነፍስ ውበት አድናቂነት መቀየር ጀምረሀል ብሎታል፡፡
 • ከመሽቀርቀር በቀር ሲያነብና ሲያስብ ተመልክቶት የማያውቀውን አቴናዊም እንዲህ ሲል መክሮታል፤ ማሰብና ማንበብ ካልጀመርክ የትኛውም ሽቶ የህይወትህን መጥፎ ሽታ ሊደብቀው አይችልም፡፡
 • ይህን ዛፍ በእጄ ይዤ ለመነቅነቅ ብሞክርም እንደማልችለው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በአይናችን የማናየው ንፋስ ሲያነቃንቀው ሲያስጨንቀው ሲያስጎነብሰው ደሞ ይውላል፡፡ የሰው ልጅም እንዲሁ በማይታይ እጅ ሲገፋና ሲናጥ የሚውል ፍጡር ነው፡፡
 • አንድ ሰው እንዴት ጥሩ ነህ ቢልህ ይህ አስተያየቱ፣ እንዴት መጥፎ ሰው ነህ ከሚለው ይልቅ ቢያስደስትህም፣ ውስጥህን በሚገባ ትመረምር ዘንድ የሚገፋህ አስተያየት ግን ቢያስከፋህ እሱ የተሻለ ነው፡፡ (አልሳደቅ)
 • አየተማረ የሚያስብ እሱ ጠፋቷል፡፡ እያሰበ የማይማር ደግሞ እሱ ታላቅ አደጋ ላይ ነው፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለፀው በተግባሩ እንጅ በንግግሩ አይደለም፤ የተግባር መሰረቱ ልዩ ፍላጎት ነውና! (ኮንፌሺየስ)
 • የአንድን ተራ ሰው ጽኑ ፍላጎት ከውስጡ ከመውሰድ፣ የአንድን ታላቅ አገር የጦር አዛዥ መማረክ ይቀላል፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • ከጥሩ ጓደኛ መቅረብ፣ ከመጥፎ ጓደኛ ደግሞ መራቅ ተገቢ አይደለምን? በማለት ሲጠይቁ፣ ከሁለቱም መራቅ ተገቢ አይደለም፡፡ ከጥሩው ጓደኛ ጥሩነቱን ሲቀዳ ከመጥፎው ደግሞ መጥፎነቱን ተመልክቼ ራሴን ማስተካከያ አደርገዋለሁ፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • በጨለማ ላይ ከማፍጠጥ እንዲት ሻማ መለኮስ ለጨለማው ችግራችን በቀላሉ መፍትሄ እናገኛለን፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • በድርጊቴም ይሁን በምግባሬ ከእኔ ጋር የሚስተካከሉ እጅግ ብዙዎች አሉ፣ ከሌሎች ለመማር ባለኝ ፍላጎት ግን ማንም አይስተካከለኝም (ኮንፌሺየስ)
 • የሀገር ጥንካሬ ከቤተሰብ ይጀምራል፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • ታላቅ ሆኖ ሳለ ታላቅነቱ ባለመታወቁ የማይናደድ ሰው እሱ በእርግጥ ታላቅ ነው (ኮንፌሺየስ)
 • አንድ ነገር መቼም ላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው! ስታውቀው ደግሞ ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው! (ኮንፌሺየስ)
 • ታላቅ ሰው ችሎታውን ለማሳየት አይሽቀዳደምም፡፡ (ኮንፌሺየስ)
 • ራስን ፈልጎ እንደማግኘት የሚያደክም ነገር የለም፡፡ (ሊያሊድ ሲስታሚን)

(ምንጭ፡- ከጥበብ መጽሐፍ፤ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ፤ ጲላጦስ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com