ዜና

የዓለምን ትኩረት እየሳበ ያለው ኢትዮጵያዊው የጃዝ ሙዚቀኛ – ኃይሉ መርጊያ

Views: 826

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ ትኩረትን እየሳበ መምጣቱን እንደ ኃይሉ መርጊያ ያሉ ሙዚቀኞች ምስክሮች ናቸው፡፡

የጃዝ ሙዚቀኛው ኃይሉ መርጊያ ለ20 ዓመታት ያህል ከሙዚቃው ዓለም ርቆ ዳግሞ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመመለስ የረዳው የአሁኑ ማናጀሩ ብሪያን ሺሞኮቪትዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅት ሙዚቃውን ሰምቶ ዳግም አልበሙ እንዲወጣ ማድረጉ እንደሆነ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር በነበረው ቃለምልልስ ላይ ይገልፃል፡፡

ለፒያኖ ልዩ ፍቅር እንዳለው የሚናገረው ኃይሉ ከሙዚቃው የራቀውም በግል ስራ ምክንያት እንደሆነም ያስረዳል፡፡

ኃይሉ ገና በ14 ዓመቱ ጦር ሰራዊት በመቀጠር ለ2 ዓመት የሙዚቃ ትምህር ተምሮ ከጨረሰ በኋላ በምሽት ክለብ በሙዚቀኛነት በኋላም የአኮርዲዮ፣ የኦርጋን ተጨዋች በመሆን ሰርቷል፡፡

በ1962 ዓ.ም አካባቢ የቀድሞ ዋሊያስ ባንድ በማቋቋም ከሂልተን ሆቴል እስከ አሜሪካን አገር ስራዎቹን ማቅረብ ችሏል፡፡

ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላም ወደ ሌላ ስራ በመሰማራት ከመድረክ ላይ ይራቅ እንጂ፣ ሙዚቃውን ጨርሶ አልተወም ነበር፤ ለራሱም ቢሆን ይጫወት ነበር፡፡

ኃይሉ ‹‹ኤርፖርት ውስጥ በታክሲ ሾፌርነት ስለምሰራ፣ በየቀኑ ልምምድ አደርጋለሁ፤ እቤት ስገባም የሙዚቃ መሳሪያዎች ስላሉኝ ማጥናት መቻሌ ዳግም ወደ ሙዚቃው ስመለስ ውጤታማ እንድሆን አድርጎኛል›› ይላል፡፡

ይህ ደግሞ እንደ አዲስ ብዙ አድናቂዎችንን እንዲያፈራ ከማድረግ አልፎ ተርፎ የተለያዩ አገሮች ጀርመን ፣ፈረንሳይ፣ ስዊድን፣ ካናዳ እና አሜሪካን ጨምሮ ስራዬን ዳግም እንዳስተዋውቅ ረድቶኛል ብሏል፡፡

ወደ ሙዚቃው ዓለም ከተመለሰ በኋላ ‹‹ላላ በሉ›› የሚል አዲስ በመሳሪያ የተቀነባበረ የሙዘቃ አልበም አሳትሟል፡፡

ለወደፊትም ቢሆን የተለያዩ አገሮች ላይ ተዘዋውሮ ለመስራት እና አዳዲስ አልበሞችን ላማሳታም ፍላጎት እና እቅድ እንዳለውም ለዋሽንግተን ፖስት ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com