የበግ ቅቅል

Views: 734

(የበግ ቅቅል ሲጥም፣

እንደ ዶሮ ቅልጥም!)

ሠላም- ሠላም ላጤዎች እንዴት ከረማችሁ!?

ዛሬ የምግብ ማብሰል ዝግጅታችንን ላቅ አድርገነዋል፡፡ ብዙ ላጤ ቅቅልን ማዘገጃጀት የትልቅ ቤተሰብ (ለባለትዳሮች) የአመጋገብ ሥርዓት ብቻ የተመቸ አድርገው ያስባሉ፡፡ ስህተት ነው፡፡ የበግ ቅቅል በቀላሉ እንዴት እንደሚዘገጃጅ አብረን ወደ ማዕድ ቤት ጎራ ብለን እንመልከት፡፡

የበግ ቅቅል ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉንን ነገሮች፡-

  • የበግ ስጋ
  • ሽንኩርት
  • ዘይት
  • ዝንጅብል
  • ነጭ ሽንኩርት
  • የስጋ መጥበሻ ቅጠል ወይም ደረቁን
  • እርድ
  • ቲማቲም
  • ቃሪያ
  • እና ቅቤ

(የሚያስፈልጉንን ሁሉ አዘጋጀን!?)

ታዲያ ለምን ወደ አሰራሩ አናልፍም፡-

የመጀመሪያው ስራችን ስጋውን በደንብ ማጠብ፤ ከቻልን ልክ እንደ ዶሮ ስጋ በሎሚ ብናጥበው ስጋውን ያጠራልናል፡፡

በጣም ጥሩ! ስጋውን አጥበን ስንጨርስ ደግሞ ድስታችንን ወይም መጥበሻችንን እንጥድና እያከታተልን መጀመሪያ ትንሽ ስጋ፣ ቀጥሎ ሽኩርቱን፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ጅንጅብል እና ነጭ ሽንኩርት እንጨምራለን፡፡

አስከትለን ደግሞ፣ ስጋ መጥበሻ፣ እርድ፣ ቲማቲም እና ዘይት እንጨምርና ለ10 ዲቂቃ ካቆየነው በኋላ 1 ሊትር ውሃ እንጨምራለን፡፡ አሁን በአግባቡ እንዲበስል ከድነን እንተወዋለን፡፡

በጣም አሪፍ! ትልቁን ስራ ሰርተናል፡፡ ከዚህ በኋላ ለ1 ሰዓት ያህል ከድነን እንዲበስል እንተወዋለን፡፡ እዚህ ጋር ግን እንዳንዘናጋ እሺ! በመሀል የጣድነውን ቅቅል ማየት መርሳት የለብንም፡፡

አሁን ቅቅላችን ደርሷል፡፡ ስንፈልግ በእንጀራ ፈትፍተን አሊያም እንዳሻን መመገብ እንችላለን፡፡  መልካም ምግብ፡፡

ታዲያ በሚቀጥለው ወዳጅዎን መጋበዝ እንዳይረሱ፡፡ ምግብ ለወዳጅነት፣ ምግብ ለፍቅር፣ ምግብ ለጤንነት፣ ምግብ ለተግባቦት፣ ምግብ ለሠላም፣ ምግብ ለሁሉም!!!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com