ዜና

በአዲስ አበባ መንግስታዊ የመሬት ወረራ እየተፈፀመ መሆኑን የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አስታወቀ

Views: 226

ምክር ቤቱ በህገ ወጥ የተገነቡ በመሆናቸው በቅርቡ ይፈርሳሉ የተባሉ ቤቶችን በተመለለከተ በፅህፈት ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው። በመጋገጫው ቤታችሁ ይፈርሳል የተባሉ ኗሪዎች ተገኝተዋል።

የማፍረስ ሂደቱ ያልተጠና መሆኑንም ምክር ቤቱ አስታውቋል። ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመላክቷል። ቤቶች ሲፈርሱ ለዜጎች የተዘጋጀ መጠለያ አለመኖሩንም ምክር ቤቱ ተችቷል።

ይህም ሀገሪቱ የፈረመቻቸውን አለም አቀፍ ሕጎች ያላገናዘበ መሆኑን የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ሰብሳቢው ጋዜጠኛ እና የዴሞክራሲ አቀንቃኝ እስክንድር ነጋ ገልጿል። ድርጊቱ ከሰብዓዊነት ውጭ መሆኑም ተነግሯል።

ድርጊቱ መንግስታዊ የመሬት ወረራ ነው ሲል ምክር ቤቱ በአቋም መግለጫው ጠቁሟል።

አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር ቤቶችን ሲያፈርስ አማራጭ መጠለያዎችን እንዲያዘጋጅ ምክር ቤቱ ጠይቋል። የተገነቡትን ማፍረሱን አቁሞ አዳዲስ ህገ ወጥ ግንባታዎች እንዳይከናዎኑ መከላከል ይገባል ሲል ምክር ቤቱ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ከሰላሳ ሺህ በላይ ቤቶችን እንደሚያፈርስ አስታውቋል። ይህም ከመቶ ሺህ በላይ ዜጎች መጠለያ አልባ ይሆናሉ እንደማለት ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com