ዜና

ከረዩ፤ አዲስ አበባ ውስጥ በቋሚነት በፌዴራል ፖሊስ የሚጠበቅ ሰፈር

Views: 293

ከረየዩ ሰፈር ከሜክሲኮ ወደ ጎጃም በረንዳ ሲሄዱ ከተክለ ኃይማኖት አደባባይ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። በአካባቢው ቢሮ ሰርተው በመኖር በቋሚነት የሚቆጣጠሩት ወይም የሚጠብቁት የፌዴራል ፖሊስ አባላት አሉት።

ሰፈሩ ውስጥ በየመቶ ሜትር ርቀቱ የማሕበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጣቢያዎች አሉ። ከ1997ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ወዲህ በልዩ የፀጥታ ቁጥጥር ውስጥ መግባቱን ኗሪዎች ተናግረዋል።

በቅርቡ በኗሪዎችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰባት የፖሊስ ባልደቦች ላይ አካላዊ ጉዳት ደርሷል። ሰፈሩን የሚቆጣጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሓላፊው እንደተናገሩት በተለይ ዓይን እና ጥርሶቻቸው ላይ ተጎድተዋል።

ከኗሪዎች መካከልም ህፃናትና አዛዎንቶችን ጨምሮ በርካቶች ተጎድተዋል። ወጣቶች ከየቤታቸው እየታደኑ በፖሊስ ተደብድበዋል።

ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በፖሊስ ባልደረቦችና በኗሪዎች መካከል ዕርቀ ሰላም ሰፍኗል። የሰፈሩ የሀገር ሽማግሌዎች እና እማዎራዎች በመገላገል የአስታራቂነት ሚናውን ፈፅመዋል።

ኢትዮ ኦንላይን በዕርቅ ስነ ስርዓቱ ላይ ቢገኝም ኩነቱን በምስልም ሆነ በድምፅ እንዳይቀርፅ በፖሊሶች ተከልክሏል። ይሁን እንጅ ከዕርቅ ስነ ስርዓቱ በኋላ የከረዩን ኗሪዎች በተናጠል አነጋግሯል። ጋዜጠኛ ሐቢብ ጌታቸው የአካባቢው ኗሪ ነው። መንግሥት ከረዩን በጦርነት ቀጠና ፈርጆታል ይላል፦

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com