የዘንድሮው ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የፈተና ኮማንድ ፖስት ሊቋቋም ነው

Views: 614

በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጠውን የ 8ኛ 10ኛ እንዲሁም የ12 ክፍል ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ ያግዛል የተባለ የፈተና ኮማንድ ፖስት ሊቋቋም መሆኑ ተሰምቷል ።

የትምህርት ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነም ኮማንድ ፖስቱ በ3 ደረጃዎች ይቋቋማል ብሏል፡፡

በከተማ አስተዳደር ፣በክፍለ ከተማ እና በትምህርት ቤት ደረጃ ለሁሉም ፈተናዎች ጥብቅ ክትትል የሚያደርጉ እንደሚሆን ቢሮ አስታውቋል፡፡

በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሚቋቋመውን ኮማንድ ፖስት በምክትል ከንቲባው ወይንም በተወካያቸው የሚመራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስለሆን የ10ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 5፤ የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 6 እስከ 11፤ የ8ኛ ክፍል ደግሞ ከሰኔ 12 እስከ 15 ይሰጣል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com