ዜና

ሠራተኛው የህብረተሰብ ክፍል የእተጨቆነ መሆኑ ተገለፀ

Views: 235

42ኛው አመት በአለም ሰራተኞች በዓል እለት የተሰው ሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት በአዲስ አበባ፤ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም እየተከበረ ነው።

በዝግጅቱ ላይ ታሪካዊ ዳሰሳ ያቀረቡት ደራሲ፣ጋዜጠኛ እና የቀድሞው ፖለቲከኛ ክፍሉ ታደሰ አሁንም ሠራተኞች ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀወል። እንደ እሳቸው አባባል ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እየተነሱ ያሉ የሠራተኞች መብቶች እስካሁን አልተመለሱም።

ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የፖለቲካ ድርጅቶችም የሰራተኛውን ጥቅም ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ተብሏል።

በበዓሉ ዝግጅት ላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ቢጋበዙም አልተገኙም። ወደ ሃያ ለሚደርሱ የመንግሥት ተቋማት ጥሪ ቢደረግም አንዳቸውም አልተገኙም።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com