ለእናንተ ለላጤዎቹ – ስጋ ጥብስ

Views: 763

ዛሬ ከእናንተ ከላጤዎች ጋር አብረን የምናበስለው ምግብ የስጋ ጥብስ ይሆናል፡፡ ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ከፆም በኋላ በመሆኑ ነው ሥጋ ጥብስን የመረጥኩት፡፡

ከሰሞኑ ለሙስሊም ወንድም- እህቶቼ ላጤዎች ደግሞ፣ ከፆም በኋላ ለሰውነት የሚስማሙ ቀለል ያሉ ምግቦችን አብረን እናበስላለን፡፡ ኢንሽ አላህ!!!

የስጋ ጥብስ ለመስራት የሚያስፈልጉን፡-

1 ስጋ በጣም መጠኑ ሳያንስ በጣምም ሳይበዛ ለጥብስ እንዲሆን በመከከለኛ ቅርፅ የተከተፈ ቢሆን ይመረጣል፤

2 መጠኑ አነስተኛ የሆነ ዘይት፤

3 ነጭ ሽንኩርት፤

4 መጠነኛ የሆነ 1 ቀይ ሽንኩርት፤

5 ቃሪያ 2 ብቻ በቂ ነው፤

6 ቲማቲም 1 ይበቃል፤

አሁን የስጋ ጥብሱን አብረን እንስራ፡-

መጀመሪያ መጥበሻችንን ትንሽ እናግልና ትንሽ ዘይት እንጨምራለን፡፡

በመቀጠል ስጋውን እንጨምር እና እንጠብሰዋለን፤ ስንጠብሰው ውሃ ስለሚኖረው ውሃው ወደ መድረቅ ሲሄድ ነጭ ሽንኩርት እንጨምራለን፡፡

ነጭ ሽንኩርቱ እና ስጋው አብረው ካባሰልን በኋላ የምናደርገው ቀይ ሽንኩርት ሳይደቅ በቁመቱ ቀጠን አድርገን እንከትፍና እንጨምራለን፡፡

ይህንን አደረግን አይደል?! ከዚህ በኋላ የሚሆነው ስራችን1 ያለደቀቀ ወይም ጎረድ ጎረድ ተደርጎ የተቆረጠ ቲማቲም እንጨምራለን፡፡

ለትንሽ ደቂቃ ቢበዛ እስከ 2 ደቂቃ እናቆየውና ቃሪያ ልክ እንደ ሽንኩርቱ ቀጠን እና እረዘም አድርገን ከትፈን እንጨምራለን፡፡

አይዞን! እየጨረስን ነው፡፡ የመጨረሻው ስራችን የሚሆነው ትንሽ ጨው ጨምረን እና ቅቤ ጣል አድርገን ማውረድ ነው፡፡ ዋው!!! ሽታው ያውዳል፡፡ በሚቀጥለው ወዳጅዎን መጋበዝዎትን አይርሱ፡፡

ይህ ጥብስ ከፈለግን በእንጀራ፣ ከፈለግን ደግሞ በዳቦ መመገብ መልካም ነው፡፡ መልካም ማዕድ ይሁንላችሁ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com