የዐማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ነገ ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያቀናሉ

Views: 382

የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎቹ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ግጭት የተፈጠረባቸውን አካባቢዎች የማረጋጋት ሥራ ለመሥራት እንደሚሄዱም ታዉቋል ።

የሁለቱ ክልል መንግሥታት የአካባቢውን ሠላም በጋራ ለማስጠበቅ መስማማታቸውን ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል ።

ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ባስነበብነዉ ዘገባ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሁኔታዎች እየተረጋጉ መሆኑን መግለጻቸውን እና ነዋሪዎች ግን ግጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መናገራቸዉን ማስታወቃችን ይታወሳል ።

Via – AMMA

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com