ዜና

አብን ኢሳትን እና ሲሳይ አጌናን በወንጀል እንደሚከስ አስታወቀ

Views: 617

የኢትዮጵያ ሳተላይት ራድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ኢሳት ‹ኢሳት በዚህ ሳምንት› በተለሰኘው የቴሌቪዥን ዝግጅቱ ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ከሆኑት አንማው አንተነህ (ዶ/ር) ጋር ባደረገው ውይይት ‹‹የአማራን ሕዝብ ሕልውና ክዷል›› በሚል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ኢሳትን፣የፕሮግራሙን አዘጋጅና አቅራቢ ሲሳይ አጌናን እና ከአማራ ምሁራን ጎራ የሚጠሩትን አንማው አንተነህን በሕግ አግባብ ሊከስ ነው፡፡

ዝግጅቱ በአማራ ሕዝብ ላይ የተሰራውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመካዱ በተጨማሪ ለወንጀለኞች ሽፋን ሰጥቷል ብሎ እንደሚያምንም አብን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አማራነትን ከክርስትና ጋር በማያያዝ አማራ የሚባል ብሔር እንደሌለ ከ27 ዓመታት በፊት አስቀድመው እየሞገቱ ነው ያላቸውን የፖለቲካ ተንታኝና የዴሞክራሲ አቀንቃኝ መስፍን ወልደማርያምንም (ፕ/ር) ጨምሮ እንደሚከስ ንቅናቄው ጠቁሟል፡፡

አንማው አንተነህ (ዶ/ር) የመስፍን ወልደማርያምን (ፕ/ር) ኃሳብ ጠቅሰው በፕሮግራሙ ላይ የራሳቸውን ኃሳብ ሲያብራሩ ተደምጠዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com