ሴቶች ሆይ፡- ተረከዛችሁን ከፍ ስታደርጉ ጤናችሁንም አስቡ

Views: 617

ሴቶች በተለያዩ ማኅበራዊ ፕሮግራሞች ላይ አምረውና ተውበው መውጣት ይፈልጋሉ፡፡ በአቅራቢያቸው ካሉ ሴቶችም፣ ትንሽ ለየትና ጎላ ብለው መታየትን ይፈልጋሉ ሲሉ የሥነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሴቶች ራሳቸውን አስውበው ከቤት ሲወጡ፤ ያላቸውን ውበት እና አለባበስ አጉልቶ እና አሳምሮ እንዲታይ ከሚመርጧቸው ጫማዎች መካከል ተረከዘ-ከፍ ያሉ (ሂል ጫማዎች)ን ይመርጣሉ፡፡

በሌላም በኩል፣ የስራቸው ሁኔታ አስገድዷቸው ዘወትር ተረከዘ-ከፍ (ሂል ጫማዎች)ን የሚያደርጉም አሉ፡፡ እነዚህ ሴቶች መቼ እና እንዴት እነዚህን ጫማዎችን ማድረግ እንዳለባቸው ማጤን ይኖርባቸዋል- ከጤና አንፃር፡፡ ተረከዘ-ከፍ ያለ ‹‹ሂል›› ጫማ የሚያዘወትሩ ሴቶች በተደጋጋሚ ማድረጋቸው የሚያርስባቸው ችግር ምንድነው?

የጀርባ ህመም ለፋሽን ብለው ተረከዙ ከፍ ያለ ‹‹ሂል›› ጫማን አዘውትረው የሚያደርጉ ሴቶች የጀርባ ህመም ያጋጥማቸዋል፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ የጫማዎቹ ምቹ አለመሆን እና ከሰውነታቸው ክብደት ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ጫና ስለሚፈጥርባቸው ነው፡፡

የጡንቻ ህመም ሌላው ሴቶች አብዝተው ተረከዙ ከፍ ያለ ‹‹ሂል›› ጫማ በመጫማታቸው የሚያጋጥማቸው የጡንቻ
ህመም ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የእግር ህመም አንዳንድ ‹‹ሂል›› ጫማዎች ሲታዩ በጣም የሚስብ መልክ እና ዲዛይን ቢኖራቸውም፣ ሴቶቹ ሲያርጓቸው
ግን ምቹነት የጎደላቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ የሀገራችን የእግረኛ መንገዶች ምቹ ናቸው ብሎ በድፍረት ለመናገር የማያስደፍሩ አባጣ-ጎርባጣ በመሆናቸው ‹‹ሂል›› ጫማ ባያዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለእግር ህመም ስለሚዳረጉ ነው፡፡

የእግር መጣመም እና ስብራት ‹‹ሂል›› ጫማ አድርጎ ከዕለት ወደ ዕለት በአስፋልት ላይ ይሁን በኮብልስቶን ድንጋይ ላይ መረማድ የእግር መጣመም ከማስከተሉ በተጨማሪ ቁርጭምጭሚት አካባቢ ያለው አጥንት እስከ መስበር ይደርሳል፡፡

የጀርባ አጥንት መጣመም ሴቶች አዘውትረው ተረከዛቸው ከፍ ያሉ ጫዎችን ሲጫሙ፣ ከሚያግጥማቸው ችግር አንዱ የጀርባ አጥንት መጣመም ነው፡፡

በአጠቃላይ የእግር ጣቶች መጣመም፣ የጉልበት ህመም እና ስብራት የሴቶቹ እግር ጫማዎቹን መሸከም ሲያቅታቸው የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው፡፡

ማድረግ ያለባቸሁ ጥንቃቄ?
1 ጫማዎቹን ስትገዙ ከውበቱ ይልቅ ምቾት ላይ አተኩሩ፤ ይህ ቢሆንም እንኳን እነዚህን ጫማዎች አዘውትረው
ባያደርጉ ይመከራል፡፡

2 በተቻለ መጠን ተቀያሪ ልጥፍ ‹‹ፍላት›› ወይም ተረከዛቸው ከፍ ያላለ እና ዘና የሚያርጎትን ጫማዎች በአማራጭነት መያዝ ስራ ቦታ ወይም ጊዜዎትን ለረዥም ሰዓት በመንቀሳቀስ የሚያሳልፉ ከሆኑ ቶሎ ቢቀይሩ መልካም ነው- ለጤናዎት፡፡

3 የምትሔዱበትን ቦታ ታሳቢ ማድረግም ይመከራል፤ በተለይ በእግር ብዙ የሚጓዙ ከሆነ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

4 የተለያየ ቦታ ለመሄድ ውጥን ካለዎትም እና ግዴታ መሄድ ካለብዎ እንደልብ ሊያንቀሳቀሰዎት የሚችትን የጫማዎችን ጫፍ ውፍረት እና ቅጥነትም ከግንዛቤ ያስገቡ፡፡ መልካም ሽርሽር!!!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com