ለላጤዎቹ – የእንቁላል ፍርፍር አሰራር

Views: 886

‹‹ላጤዎች›› ምግብ ለማብሰል የሚቸገሩት ብዙ ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ ስለማያሳልፉ በተሞክሮ ማነስ
ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም፣ ቀደም ሲል በትልቁ ቤተሰብ ውስጥ ሲኖሩ፤ ምግብ አብስለው የማያውቁ ሰው ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እንዲህ ዓይነቱን ‹‹ላጤ›› ብዙ ሰዓት የማይወስድበትን (የማይወስድባትን) የምግብ ዝግጅት
ማሳወቅ ቁምነገር ይሆናል፡፡ ስለዚህ፣ ለዛሬ በአጭር ጊዜ የሚደርስ፣ የአንድን ሰው የምግብ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል
የእንቁላል ፍርፍር አሰራር እንመልከት፡፡

የሚስያፍልጉን የምግብ ፍጆታዎች፡-
4 እንቁላል
1 ሽንኩርት
መጠነኛ ዘይት
1 ወይም 2 ቲማቲም
2 ቃሪያ ብቻ፡፡

አሁን አብረን ምግባችንን እናዘጋጅ፡-
መጀመሪያ ሽንኩርቱን በምንፈልገው መጠን መክተፍ፤ ቀጥለን ደግሞ እንቁላሉን ሰብረን በጎድጓዳ ሰሃን
ውስጥ መጨመር፡፡

በመቀጠል፣ እንቁላሉ አረፋ እስኪያወጣ ድረስ ትንሽ ጨው እና በቤታችን ውሰጥ ቁንዶ በርበሬ ካለን የተወሰነ
ቁንዶ በርበሬ ጨምረን አንድ ላይ እንመታዋለን፡፡

ይህንን አድርግን ከጨረስን በኋላ፣ ቀጥሎ የሚሆነው ስራርችን፡-
መጥበሻችን መጣድ፤ ዘይት መጨመር፤ በመቀጠል ሽንኩርት መጨመር፤ ከዚያም ቲማቲም (የምንፈልግ
ከሆነ ብቻ ነው የምንጨምረው) ከዚህያ በመቀጠል ደግሞ የመታነውን እንቁላል ወደ መጥበሻው ጨምረን እያማሰልን
ማበሳሰል ነው፡፡ የመጨረሻው ስራችን የሚሆነው ደግሞ ቃሪ ጨምሮ ማውረድ ብቻ ነው፡፡ ዋው ሽታው ያውዳል!!!
አሁን ለመመመገብ ዝግጁ ነዎት፤ መልካም ምግብ ይሁንልዎት፡፡ በሚቀጥለው ወዳጅዎን መጋበዝ ይችላሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com