ዜና

አቶ ጌቱ አርጋው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

Views: 829

አቶ ጌቱ የተሾሙበት ትክክለኛ ቀን ባይገለፅም ኃላፊነታቸውን በዛሬው ዕለት በይፋ መረከባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። አቶ ጌቱ አርጋው ከዚህ ቀደም በድሬደዋ የኢሕአዴግ ኮሚቴ ፅሕፈት ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የደኢሕዴን አስተባባሪ ሆነው አገልግለዋል። በኃላፊነታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ተጀምረዋል ያሏቸውን የለውጥ ሥራዎች አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ አቶ ጌቱ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል በተካሔደው መርሐ-ግብር ከሹመታቸው የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ሥጦታ እንደተበረከተላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል። በድንገት ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ የዋና ከተማዋን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩ አቶ ይሕደጎ ሥዩምን ተክተው የተሾሙት ባለፈው ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር።
(ፎቶ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com