ለላጤዎቹ (ክፍል 2)

Views: 264

ዛሬ ደግሞ ላጤዎች በቀላሉ በቤታቸው ውስጥ ሊሰሩት የሚችሉትን የ‹‹ፓን-ኬክ›› አሰራር
እንነግሯችኋለን፡፡

ለአንድ ሰው የሚበቃ ፓን-ኬክ ለመስራት የሚሳፈልጉን ነገሮች፡-

  1. የሩብ ግማሽ ፍርኖ ዱቄት
  2. ግማሽ ኩባያ ውሃ
  3. 2 ሲኒ ወተት ወይም ውሃ (ውሃው ለፆመኞች)
  4. 1 እንቁላል
  5. 1 ሾርባ ማንኪያ ቫኔላ
  6. 3 ማንኪያ ስኳር
  7. ጨው በሁለት ጣታችን ብንመጥን ይበቃናል፡፡
  8. 1 ማነኪያ ቤኪንግ ፓውደር

ወደ አሰራሩ ስንሄድ፡-
በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ዱቄቱን መጨመር፤ በመቀጠል ግማሹን ወተቱን መጨመር ወይም ውሃውን፤ ይህንን ካደረግን በኋላ፣ እንቁላን እንሰብርና እንጨምርበታለን፤ ከዚህ በኋላ የቀረውን ወተት እንጨምር እና እናዋህደዋለን፡፡

ይህንን አድርገን ከጨረስን፣ መጥበሻችንን ዘይት እንቀባውና የተዋሃደውን ፓን-ኬክ በመጥበሻው ላይ እንጋግረዋለን፡፡ ትንሽ እናቆየውና፣ እንገለብጠዋለንትን፤ ትንሽ እናቆየዋለን፤ ይህን አደርገን ስንጨርስ- እናወጣዋለን፡፡

አሁን ለመመገብ ዝግጁ ናቸሁ፡፡ መልካም ምግብ!!! በሚቀጥለው እጮኛዎን መጋበዝኦትን አይዘንጉት፡፡
ፍቅርና አክብሮት ይጨምራል፡፡ መልካም ቀን-ምሽት!!!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com