ለላጤዎቹ

Views: 250

ከቤተሰብ ሕይወት ተላቀው የግል ሕይወት የጀመሩ ላጤዎች፣ በህይወት ውስጥ ካሉባቸው ተግዳሮቶች አንዱ አብስሎ መመገብ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ብዙ የሙያ ተሞክሮና ወጪ ያልበዛባቸው በቀላሉ ሊሰሩ የሚችሉ የምግብ አሠራር እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸው እናሳውቃለን፡፡

የሚያስፈልጉን ነገሮች፡-

  1. ጥቂት ድንች
  2. ትንሽ ካሮች
  3. መጠኘኛ ፎሰሊያ
  4. የተወሰነ ሽንኩርት …

አሰራሩን ስናይ ደግሞ፣ መጀመሪያ ካሮት መላጥ፣ በመቀጠል በ4 ማዕዘን ከከተፍን በኋላ በሰሃን እናስቀምጠዋለን፡፡
ቀጥሎ ድንች እንልጥና ልክ እንደ ካሮቱ በአራት መዓዘን ከትፎ በሰሃን ማስቀመጥ፡፡

ይህን ካደረግን በኋላ፣ ፎሰሊያውን ጫፍ እና ጫፍ ያሉትን ጭራ መሰል ነገሮች ማስወገድ፤ በመቀጠል ከድንቹና ካሮቱ ቅርፅ ጋር በማነጻፀር መክተፍ፡፡

ይህንን አድርገን ከጨረስን፣ ቀጣዩ ስራችን የሚሆነው ደግሞ በድስት ውሃ ትንሽ መጠን ያለው ጨው እንጨምርና እንጥደዋለን፡፡
ውሃው ሲፈላ፣ ድንቹን እናገነፍለዋለን፡፡

ድንቹን ካጠነፈፍን በኋላ፣ ውሃውን ደግመን እንጥደውና ካሮቱን እናገነፍለዋለን፤ ልክ ይህን አድርገን ከጨረስን በኋም፣ ፎሰሊያውን በድንቹና በካሮቱ መልክ ካገነፈልን በኋላ ማስቀመጥ፡፡

ቀጣዩ ስራችን ድስት መጣድ ይሆናል፤ ቀጥሎ ዘይት መጨመር፣ ከዚህ በመቀጠል ቀይ ሽንኩት (ካለን ከነጭ ሽንኩርት) ጋር አቀላቅለን መጥበስ፡፡ ይህንን ካደረግን በኋላ፣ መጀሪያ ፎሰሊያውን መጨመር፤ ቀጥሎ ካሮት እና ድንቹን ጨምረን፤ (ከላን) ቁንዶ በርበሬ እና ጨው ጨምሮ ትንሽ ከጠበስነው በኋላ ማውረድ፡፡

ዋው ጥዑም ምግብ፤ አሁን ለመመገብ ዝግጁ ነዎት፡፡ መልካም ምግብ ይሁንልዎት፤ በቀጣይ ወዳጅኦን መጋበዝ ይችላሉ፡፡
ሌላ እንድነግርኦት የምትፈልጉት የምግብ አሰራር ካለ ‹‹ኮሜንት›› ላይ ገብታቸሁ ፃፉልን እናመሰግናለን፡፡ መልካም ምግብ! ሰው የተመገበውን ይመስላል- ይባላል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com