ዜና

የአልጄሪያው ፕረዚዳንት አብዱልአዚዝ ቡተፍሊካ ሥልጣን ለቀቁ

Views: 282

የአገሪቱ ቴሌቭዢን እንደዘገበው አብዱልአዚዝ ቡተፍሊካ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለሀገሪቱ ህገመንግስታዊ ምክርቤት አቅርበዋል ።

አልጄሪያን ለ 20 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሯት የ 82 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ቡተፍሊካ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው የጤና ዕክል ላይ እያሉ እንኳን ለ 5ተኛ ዙር ምርጫ ለመካፈል ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ ነዉ ።

አዛዉንቱ እ.አ.አ ከ 2013 ጀምሮ በስትሮክ በሽታ ተይዘዉ ህክምና ላይ መሆናቸው ይታወቃል ።

Via EBC

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com