ዜና

ኦሮሞዎች ከኦሮሚያ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ተርበዋል

Views: 266

ከኦሮሚያ ክልል ከጉጂ ዞን ከመቶ የሚልቁ ኦሮሞዎች ተፈናቅለው አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ እነዚህ የኦሮሞ ተወላጆች ከልዩ ልዩ የአሮሚያ አካባቢዎች ሄደው ሥራ እና ኑሯቸውን በሻኪሶና አካባቢው አድርገው እንደነበር ገልፀውልናል፡፡ ተፈናቃዮቹ ከስድስት ቀናት በፊት ጀምሮ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት አስፋልት መንገድ ጥግ ያረፉ ሲሆን ከርሃብ ጋር ሲታገሉ ውለው እንደሚያድሩ ተናግረዋል፡፡ ሕፃናት፣አዛውንቶች እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ ሰውነታቸው በርሀብ ደክሞ ተመልክተናል፡፡ የተፈናቀሉት ከአስራ ስምንት ቀናት በፊት ሲሆን አዲስ አበባ የደረሱት በእግራቸው በመጓዝ፤ አልፎ አልፎም ከመንገደኞች የተሽከርካሪ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ለኢትዮ ኦን ላይን አብራርተዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ‹‹መንግሥት የነፍስ ደራሽ ድጋፍ እንዲያደርግልን ብንጠይቅም አልደገፈንም፡፡ ያረፍንበትን አካባቢ ለቀን እንድንሄድ የኦሮሚያ ፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት አዝዞናል፡፡›› ብለዋል፡፡ ምግብ ከመንገደኛ ለምነው እንደሚበሉም ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ መረጃውን እንዳገኘን ምላሻቸውን አካተን ተጨማሪ ዘገባ እናቀርባለን፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com