ዜና

አሜሪካ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥታው የነበረው ህግ እንዲቀጥል ወሰነች

Views: 41

በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተፈረመው ይህ ህግ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ነው

በህጉ መሰረት በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያዛል

አሜሪካ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥታው የነበረው ህግ እንዲቀጥል ወሰነች።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከአንድ ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ህግ አዘጋጅተው ነበር።

አሜሪካ ይሄንን ህግ ማውጣቷን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና በውጭ ሀገራት ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን “በቃ” ወይም “NOMORE” በሚል  ህጉ ሊቀር ይገባል የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት የዲፕሎማሲ ጥረት ይህ ህግ በጊዜያዊነት ቆሞ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ ይህ ህግ ከወጣበት ከፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር ከመስከረም 17 ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ እንዳዘዙ የነጩ ቤተ መንግስት ድረገጽ ያስረዳል።

አሜሪካ ይሄንን ህግ የዘጋጀችው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የኢትዮጵያን ፣ምስራቅ አፍሪካን እና የአሜሪካንን ብሄራዊ ጥቅም ይጎዳል በሚል እንደሆነ አስታውቃለች።

በዚህም መሰረት ጦርነቱ  እንዲቀጥል በሚያደርጉ፣ ለዜጎች እርዳታ እንዳይደርስ በሚያስተጓጉሉ እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ የውጭ ሀገራት አካላት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አሜሪካ አስጠንቅቃለች።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

የፌደራል መንግስት እና ህወሓት ለወራት ቆሞ የነበረውን ጦርነት መጀመሩን ባወጡት ባሳለፍነው ወር ነሃሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ መከላከያ ሰራዊትና እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃይሎች ትግራይ ደቡባዊ አቅጣጫ ባለው ግንባር በኩል ተኩስ መክፈታቸውን አስታውቋል።

የህወሓት መግለጫን ተከትሎ የፌደራል መንግስት ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ሰዓት በተያየ አቅጣጫ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል።

የፌደራል መንግስት በሽብርተኝነት ከፈረጀው ህወሓት ጋር ያለውን ግጭት በድርድር ለመፍታት ማስታወቁ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚደረደር መግለጹ ይታወሳል። ህወሓትም በተመሳሳይ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ ነበር።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *