ዜና

ቻይና በትንፋሽ የሚወሰድ የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች

Views: 47
ቻይና በትንፋሽ የሚወሰደው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጥታለች፡፡
የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱ ካንሲኖ በተሰኘው የቻይና የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የተመረተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ክትባቱ በመርፌ ከሚሰጠው ክትባት ጋር ተመሳሳይ ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን÷የኮሮና ቫይረስን ለመካከል ጥሩ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የቻይና ብሔራዊ የመድሃኒት ምርቶች አስተዳደርም ካንሲኖ የተሰኘው እና በትንፋሽ የሚወሰደው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት አገልግሎት ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይህም ቻይና በትንፋሽ የሚወሰደውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል ነው የተባለው፡፡
የአሜሪካ እና ብሪታኒያ ተመራማሪዎችም በአፍንጫ የሚወሰዱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባቶችን ለመስራት ምርምር እያካሄዱ መሆናቸው በዘገባው ተጠቁሟል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *