ዜና

ለላቀ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ዕውቅና የሚሰጥበት የ”ሆሄ” የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት ተካሄደ

Views: 43
ለላቀ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ዕውቅና የሚሰጥበት የ”ሆሄ” የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት ለአራተኛ ጊዜ ተካሄደ።
አራተኛው ሆሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት “ዳበራ! ለዕውቀት ጎታ!” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ነው የተካሄደው።
የሆሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት የቦርድ አባል ኤፍሬም ብርሃኑ፤ የሽልማቱ ዓለማ ለላቁ የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች ዕውቅና ለመስጠት መሆኑን ገልፀዋል።
መጽሐፍ ለማፃፍ አስበው ያልፃፉ፣ የፃፉትን ማሳተም ላልቻሉና በሌሎች ምክንያቶች መሰናክል የገጠማቸውን ለማበረታታት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የሥነ- ጽሑፍ ዘርፍ የአንድን ሀገር ሕዝብ ቋንቋ፣ ባህልና ፍልስፍና መጎልበት የላቀ ድርሻ ያለው በመሆኑ የማበረታታቱ ስራ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
የዘንድሮው የሁሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት በ2011 ዓ.ም ለህትመት የበቁ መጻሕፍት እንዲሽለሙ የተደረጉ መሆኑን ጠቅሰው ሽልማቱ በወቅቱ ሳይካሄድ በመቅረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ በ10 የተለያዩ ዘርፎች ሽልማት መበርከቱን የገለጹት አቶ ኤፍሬም በአጭርና ረዥም ልቦለድ፣በግጥም፣ በግለ ታሪክ፣ በጥናትና ምርምር፣ በልጆች መጽሐፍ፣ በሥነጽሑፍ የሕይወት ዘመን ባለውለታ በሚል ተከናውኗል አስረድተዋል።
በማኅበራዊ ዲጂታል ሚዲያ መጽሃፍትን ለአንባቢያን ተደራሽ ማድረግ፤ ሥነ-ጽሑፍን ለማኅበራዊ ግልጋሎት በማዋልና ለአካል ጉዳተኞች አካታች ፕሮግራም ማካሄድ የሚሉ የሽልማት ዘርፎች ተካተውበታል።
የሆሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት በ2009 ዓ.ም ተጀመረ ሲሆን በዘንድሮው በመጻሕፍት ዘርፍ ስድስት፣ አንድ የሕይወት ተሸላሚና ሦስት ለሥነ-ጽሑፍ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *