ዜና

ሊዝ ትረስ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

Views: 40
የ47 ዓመቷ ሊዝ ትረስ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በንግስት ኤልዛቤት ተሾሙ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ከሥልጣን መልቀቅ ተከትሎ፥ እሳቸውን ለመተካት በወግ አጥባቂ ፓርቲው ውስጥ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ አብላጫ ድምጽ ያገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሊዝ ትረስ ትናንት የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
ሊዝ ትረስ በስድስት ዓመታት ውስጥ የአገሪቱ ወግ አጥባቂ ፓርቲ አራተኛዋ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተገልጿል።
የ96 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤጥ፥ ሊዝ ትረስን ተቀብለው ያነጋገሯቸውና የመንግስት አስተዳደራቸውን እንዲመሰርቱ ትዕዛዝ መስጠታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *