ዜና

በመዲናዋ በጎርፍ አደጋ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ባለ 2 መኝታ ቤትና 150 ሺህ ብር ተበረከተላቸው

Views: 39
በመዲናዋ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ሁለት ልጆቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለ 2 መኝታ ቤትና የ150 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገላቸው፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ÷ “ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው፤ አስተዳደራችን በሚችለው ሁሉ ከጎናችሁ ነው፤ ያጣችኋቸውን ልጆቻችሁን መመለስ ባንችል እንኳን መፅናኛ ይሆናችሁ ዘንድ ይህን ድጋፍ አድርገንላችኋል” ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ÷ ስጦታው ክፍለ ከተማው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ያበረከተው ስጦታ መሆኑን ገልፀው መጭውን አዲስ ዓመት ሀዘናችሁን ቀንሳችሁ ተደስታችሁ መዋል ይገባችኋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሁለት ልጆቻቸውን በጎርፍ አደጋ ያጡት እናት ወይዘሮ ረውዳ ጀማል በበኩላቸው÷ አስተዳደሩ ላደረገላቸው ገንዘብና የቤት ስጦታ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *