ዜና

ሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚሄድውን የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር እከፍታለሁ ያለችበትን ቀነ ገደብ ሰረዘች

Views: 36

በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ በ400 በመቶ መጨመሩ በኢንዱስትሪዎች ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው

ሩሲያ በፈረንጆቹ መስከረም ሶስት ያቋረጠቻቸውን እና ወደ አውሮፓ ጋዝ የሚወስዱ ትላልቅ መስመሮችን ለመክፈት ያስቀመጠችውን ቀነ ገደብ መሰረዟን አስታውቃለች፡፡

ቀነ ገደቡን ላለማክበር ሩሲያ እንደምክንያት ያስቀመጠችው በኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጥገና በሚደረግበት ጊዜ ብልሽት ከደረሰበት በኋላ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ክስተቱ በአውሮፓ ያለውን የክረምት ወቅት ጋዝ አቅርቦት ይጎዳዋል ተብሏል፡፡

ለጀርመን እና ሌሎች ሀገርት ጋዝ የሚያቀርበው እና በባልቲክ ባህር ስር የተዘረጋው ኖርድ ስትቲም 1 ለሶስት ቀናት ጥገና ከተዘጋ በኋላ በዛሬው እለት መከፈት ነበረበት፡፡

ንብረትነቱ የሩሲያ መንግስት የሆነው የነዳጅ ኩባንያ ጋዝ ፕሮም በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተገኘው ፍስት ካልተስተካከል ጋዝ ማቅረብ እንደማይችል አስታውቋል፡፡ ኩባንያው መስመሩን ሊከፍት የሚችልበት ጊዜ ገደብ አልለጸም፡

የጀመርመን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስብሳቢ እንደተናሩት የኩባንያው ምክንያት ሩሲያ በጀርመን ላይ ከከፈተችው ስነልቦና ጦርነት አካል ነው ሲሉ ጽፈዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኃላፊ ኡርዙላ ቮን ደር ለይን እንደተናሩት በማስተላለፊያ መስመሮቹ በሚጓጓዝ ነዳጅ ላይ ዋጋ ተመን መቀመጥ አለባት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሀምሌ ወር በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ በ400 በመቶ የጨመረ ሲሆን ይህም አውሮፓን ኢንዱስትሪ እና ቤተሰቦች ላይ ጉዳ አድርሷል፡፡

ቀደም ሲል በኮሮና ምክንያት ችግር ውስጥ ለነበረው አውሮፓ ኢኮኖሚ ተጨማሪ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ምእራባውን ሀገራት በሩሲያ ላይ በሽዎች የሚቆጠሩ ማእቀቦችን ጥለዋል፡፡ ሩሲያም በጋዝ ምርት አቅርቦቷ ላይ የተለያዩ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ነች፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *