ዜና

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የዶክተር ቴድሮስን የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ድርጊትን እንዲያስቆም ጠየቀች

Views: 47
ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከተቋሙ ሰራተኞች ሥነ ምግባር በተፃረረ መንገድ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ድርጊትን እንዲያስቆም በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያን ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት ጠየቀ።
ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ በፈረንጆቹ ኅዳር 3 ቀን 2020 አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታዉሶ ፤ጥቃቱን ተከትሎ ከሕወሓት አመራሮች አንዱ የሆነዉ ዶክተር ቴድሮስ በሕወሓት የቁጥጥር ሠንሠለት ሥር ሆኖ ትዕዛዝ በመፈፀም የሽብር ቡድኑን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሠራጭ መቆየቱን አመላክቷል፡፡
ሕወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትን፣ የህዝብ አገልግሎት ተቋማትን እና መሠረተ-ልማቶች ሲያወድም ዶክተር ቴዎድሮስ ሲያወግዝ አለመታየቱን መግለጫዉ ጠቁሟል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ አብዝቶ የሚደግፈው ይህ ቡድን አሁንም በአጎራባች ክልሎች ላይ የፀብ-ጫሪ ተግባሩን መቀጠሉን አመላክቷል፡፡
ባለፈው ወረራ የፈጸማቸውን የህዝብ ተቋማት የማውደም ፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን የመፈጸም እና የመጨፍጨፍ ተግባራት አሁንም በክልሎቹ መቀጠሉንም አውስቷል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ ያለውን ስልጣን የኢትዮጵያን መንግስት ስም ለማጥፋት እየተጠቀመ መሆኑን ያመለከተዉ መግለጫዉ በዚህም ተግባሩ የዓለም ጤና ድርጅት መልካም ስምን፣ ገለልተኝነት እና ተዓማኒነት ክፉኛ መጉዳቱን አስታውቋል፡፡
ይህ የዓለም ጤና ድርጅት የሰራተኞች ስነ ምግባር ደንብን የጣሰዉን የዶክተር ቴዎድሮስ ድርጊትን የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በፍጥነት እንዲመረምር ጠይቋል።
በአንድ አባል አገር ላይ ከፍተኛ በደል መፈፀሙን በማመልከት የኢትዮጵያን ቅሬታን ለቦርዱ ማስገባቱን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *