ዜና

ሁመራ ከተማ በተረጋጋ ሁኔታ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገለፁ

Views: 37
ዶቼ ቬለ DW ዛሬ ቀን ላይ ያነጋገራቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ በህወሓት እና በኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት መካከል ዉጊያ ካገረሸ ወዲህ በአካባቢው በረከት እና ሸረሪና በሚባል ቦታ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።እሳቸው የሚኖሩበት ሁመራ ከተማ ግን በተረጋጋ ሁኔታ ህይወት በተለመደው ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
ነዋሪው እንደሚሉት ጠዋት ላይ የመሳሪያ ድምጽ ከሩቅ ይሰማ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን ምንም ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።
በአካባቢው ውጊያው የተደጀመረው ሌሊት ሲሆን፤ እሳቸው ግን የሰሙት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። የእሳቸው የእርሻ ቦታ በረከት አካባቢ ሸረሪና የሚባል ቦታ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ነዋሪው አያይዘውም ህብረተሰቡ ወደ ውጊያ ቦታ ለመሄድ ነቅሎ ነው የወጣው መከላከያ በቂ ነው ያለው ተብሎ ከምድራዊ ከምትባል ቦታ ነው የተመለስ ነው።
ማህበረሰቡ ለሰራዊቱ የተለያዩ ምግብ እና ውሃ ጭኖ እያደረሰ መሆኑንም ነዋሪው በስልክ ገልፀዋል።
ያም ሆኖ በሚኖሩበት በሁመራ ከተማ «ህይወት እንደ ቀጠለ ነው። ሁሉ ነገር እንደበፊቱ ነው።» ብለዋል ።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *